ከተመሠረተ አምስት አመት ያስቆጠረው ኮስሞፖሊታን ሪል እስቴት በከተማዋ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግርንም ለማቃለል በማሰብ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ያስገነባውን ጂ ኘላስ 11 የሆነ በ 700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ አፖርታማ በዛሬው እለት አስመረቀ።
ህንፃው የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም፣ ሳውናና ስቲም የተሟላለት የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ የተመቻቸላቸው በሙያው የላቀ ልምድ ባካበቱ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሙያዎች የተገነቡ ሲሆን የቤቶቹ የአሠራር ጥራት ደረጃውን የጠበቀ እና ዋጋቸውም ተመጣጣኝ ናቸው ተብሏል።
ኮስሞፖሊታን ሪል እስቴት በአሁኑ ሰዓት በአገራችን በቤቶች ግንባታ እና በሌሎች ዘርፎችም ላይ ተሠማርቶ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ኦሎምፒያ ጂ+17 ህንጻ እንዲሁም በፒያሳ ካቴድራል አካባቢ ለሱቅና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የገበያ ማዕከል ግንባታ የሚጀምር ሲሆን ይህም ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን የስራ ዕድል ይፈጥራል ከዚህ ፊት በሶስቱ ፕሮጀክቶች ለ25ዐ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።
በአስመጪና ላኪነት፣ በቤት እና በቢሮ እቃዎች፣ በወረቀት ማምረት እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሠማራው ኮስሞፖሊታን ለደንበኞቹ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት ቀዳሚ ግቡ በማድረግ እየሰራ ይገኛል።