ኢን- ጆይ በርገር የአንድ ሚሊዮን ብር ስጦታ ሰጠ።

Reading Time: 2 minutes

በፈጣን ምግቦች በማቅረብ እና ቅርንጫፎቹን በማስፋት ላይ የሚገኘው ኢን-ጆይ በርገር ለአራት የበጎ አድራጎት ተቋም ለእያንዳንዳቸው የ250ሺህ ብር በድምሩ የአንድ ሚሊዮን ብር የገንዘብ ስጦታ በዛሬው እለት አበርክቷል።

ላለፉት ሁለት ወራት “የክረምት በርገር ፌስቲቫል ” በሚል በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 8 ቅርንጫፎች ሲካሄድ የነበረው ልጆችን እና ቤተሰብን አሳታፊ ጨዋታዎች የማጠናቀቂያ መርሃግብር ሰሚት በሚገኘው የኢን-ጆይ በርገር ቅርንጫፍ ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2016 ዓ.ም ተከናውኗል።

ኢን-ጆይ በርገር በአፍሪካ ትልቁ የፈጣን ምግብ አቅራቢ ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት የድርጅቱ ባለቤት እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሳለአምላክ አንዳርጌ በቅርቡ በክልል ከተሞች እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ እና በመካለኛው ምስራቅ ሀገራት ቅርንጫፎቹን ለመክፈት በሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በዛሬው የክረምት በርገር ፌስቲቫል ማጠናቀቂያ መርሐግብር ላይ ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ፣ ለሙዳይ የበጎ አድራጎት ፣ ለመሠረት ፋውንዴሽን እና መቀመጫውን ጎንደር ከተማ ላደረገው የቀድሞ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መርጃ ድርጅት ለተባሉ ልጆች ላይ እየሰሩ ለሚገኙ የበጎ አድራጎት ተቋማት ለእያንዳንዳቸው የ250ሺህ ብር በድምሩ የአንድ ሚሊዮን ብር የገንዘብ ስጦታ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በፌስቲቫሉ ማጠናቀቂያ መርሐግብር ላይ የኢን-ጆይ በርገር ደንበኞች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የበጎ አድራጎት ተቋማት ተገኝተዋል።

ከተመሠረተ 13 አመታትን ያስቆጠረው ኢን-ጆይ በርገር ከ350 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞች ቋሚ የስራ እድል ፈጥሯል።

59790cookie-checkኢን- ጆይ በርገር የአንድ ሚሊዮን ብር ስጦታ ሰጠ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE