እናት ባንክ ለ60 እናቶች ቤተሰባዊ የበዓል ስጦታ አበረከተ !

Reading Time: < 1 minute
እናት ባንክ ከ”እንደዜጋ ማህበራዊ እንደራሴ” ከተሰኘ አገር በቀል ድርጅት ጋር በጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ የጎዳና ፅዳት ላይ ለሚሰሩ እና ከዚህ ቀደም የ”እናት ለእናትን”ስልጠና ለወሰዱ 60 እናቶች፤ “ቋይእቶን” የተሰኘ፤ የእቶንን እና የቋያን ጥምር ቃል የያዘ የከሰል ማንደጃ መጪውን የመውሊድ እና የመስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ የበዓል ስጦታ ካሳንቺስ በሚገኘው እናት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ትናንት መስከረም 12 ቀን 2016 ዓ.ም የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አበርክቷል።

ከስጦታው መርሐግብር ባሻገር እናት ባንክ የእናቶቹን የገቢ አቅም ማሳደግ እና በዘላቂነት በኢኮኖሚ ለማብቃት ዓላማ ያደረገ የሦስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ከእንደ ዜጋ እና አነጋ ኢንጅነሪንግ ከተሰኙ ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት ተፈራርሟል።

እናት ባንክ ከተመሠረተበትና እየተገበረ ካለው የተሟላ የባንክ አገልግሎት አቅርቦት በተጓዳኝም ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር በመሥራት ማኅበረሰብን የመጥቀም አካሔድ ወደፊትም ዘርፈ ብዙና ለተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚጠቅሙና ችግር ፈቺ በሚሆኑ ሥራዎች ላይ በስፋት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

59770cookie-checkእናት ባንክ ለ60 እናቶች ቤተሰባዊ የበዓል ስጦታ አበረከተ !

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE