ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ኤጂ ግሬስ የንግድ ማዕከል ተመረቀ።

Reading Time: 2 minutes
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ አዱሱ አደይ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት የተገነባው ባለሁለት ቤዝመንት እና ግራውንድን ጨምሮ ባለ 20 ወለል ያለውን ሁለገብ ህንጻ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፥ የንግዱ ማህበረሰብ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል።

ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ኤጂ ግሬስ የንግድ ማዕከል ህንጻ ለንግድ ፤ ለቢሮ፣ ለስልጠና ማዕከላት፣ ለአዳራሽ፣ ቅንጡ አፓርትመንቶች እና ለተለያዩ አገለግሎቶች የሚውሉ ምርጫዎችን ያካተተ ሲሆን ለበርካታ የከተማችን ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ ነው፡፡

በምርቃቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የህንጻው ባለቤት አቶ በረከት ከበደ እንደገለጹት ላለፉት 6 አመታት ኤጂ ግሬስ ህንጻን በግንባታ ሂደት ላይ ሃሳብ በማመንጨት፣ በእቅድ ውስጥ በመሳተፍ፤ እውቀታችሁን እና ጊዜያችሁን በመስጠት በሌለንበት ጊዜ ሁሉ እንደ ባለቤት ኃላፊነታቸችሁን ሲወጡ ለነበሩ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኤጂ ግሬስ የንግድ ማዕከል በቀጣይ በኤክስፖርቱ ዘርፍ አሁን ከእኛ ጋር ሽርክና ካላቸው የንግድ ተቋማት ጋር በመጣመር የውጭ ምንዛሪ ወደ አገራችን ማስመጣት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረት እና ሰፊ የስራ እድልን ለመፍጠር የታቀደ ሲሆን አለም አቀፍ መመዘኛን ያሟሉ የተለያዩ ኢንተርናሽናል የንግድ ተቋማት፣ የመዝናኛ ማዕከላት፣ ሬስቶራንቶችና ካፌዎች፣ የቴክኖሎጂና የስልጠና ማዕከላትና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ተቋማትን የሚያካትት የገበያ ማዕከል ለመገንባት እና በአገራችን ያለውን የመኖርያ ቤት እጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን ዜጎቻችንን ያማከሉ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት በሪል ስቴት ዘርፍ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ አቶ በረከት ከበደ ገልጸዋል።

59750cookie-checkከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ኤጂ ግሬስ የንግድ ማዕከል ተመረቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE