ሄርሜክስ ትሬዲንግ የአዲስ ዓመት በዓልን አስመልክቶ አቅመ ላጠራቸው ወገኖች የበዓል ስጦታ አበረከተ።

Reading Time: 2 minutes
በርካታ አጋዥ የሌላቸውን ልጆች እያስተማረ የሚገኘው የሄርሜክስ ትሬዲንግ ባለቤት ወጣቱ ባለሀብት ሄርሞን ሀጎስ አዲስ አመትን በማስመልከት በዛሬው ዕለት ጳጉሜ 6 ቀን 2015 ዓ.ም ሜሪጆይ በገዳም ሰፈር ወረዳ 6 ግቢ ውስጥ በተገነባው የጎዳና ልጆች ህጻናት ማቆያ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ተገኝቶ ከ100 በላይ የሚሆኑ አረጋውያንን እና ህጻናትን ምሳ በመጋበዝ ለበአል መዋያ 250 ሺ ብር ድጋፍ አድርጓል።

ያለንን ማካፈል ይህ የመጀመሪያችን ሳይሆን ከእዚህ በፊትም ስናደርገው የነበረ ቢሆንም በዛሬው ዕለት እነዚህን አረጋውያኖች እና ህጻናትን መጎብኘት መቻላችን እና ያለችን ማካፈል መቻላችን ደስ አሰኝቶናል። ወደፊትም በቻልነው አቅም ሁሉ ከጎናችሁ ነን በማለት ሄርሞን ሀጎስ ተናግሯል።


በተጨማሪም የሀገራችን ባለሀብቶች ለተቸገሩ ወገኖቻችን ያላቸውን በማካፈል ለወገን ደራሽ የመሆን ባህላቸውን እንዲያዳብሩ መልዕክቴን ማሥተላለፍ እችላለሁ ብሏል።

ሄርሞን ከእዚህ በፊት በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረጉ የተለያዩ ሽልማቶችን ተሸልሟል።

ሜሪ ጆይ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል መስራች ሲስተር ዘቢደር ይህን ከተመሠረተ ከ30 አመት በላይ ያስቆጠረውን ድርጅታቸውን ያገዘውን ሄርሞንን አመስግነዋል።

እንዲሁም በዶክተር ዮናስ የተበረከተላቸውን ቤት ለጎዳና ልጆች ማቆያ አድሰው በዛሬው እለት ያስመረቁ እና ስራ ያሥጀመሩ ሲሆን ለእዚህ እድሳት ከጎናቸው የነበሩትን በሙሉ አመሥግነዋል።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በ1986 ዓ.ም. በህግ የተቋቋመ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ላለፉት 30 ዓመታት በርካታ የልማት ስራዎችን ማከናወን የቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጣም አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የህፃናት እናቶች እና ወጣቶች ለጎዳና ህይወት ተጋላጭነት ለመግታት በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

59520cookie-checkሄርሜክስ ትሬዲንግ የአዲስ ዓመት በዓልን አስመልክቶ አቅመ ላጠራቸው ወገኖች የበዓል ስጦታ አበረከተ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE