በአል በመጣ ቁጥር በውጭ የሚኖሩ ወዳጆቹን እና የኪነ ጥበብ ባለሙያ ጓደኞቹን በማስተባበር ለተቸገሩ ወገኖቻችን የበዓል መዋያ ገንዘብ በመስጠትና ከተቸገሩት ጋር በአልን በማሳለፍ የሚታወቀው ፕሮሞተር ሰለሞን ገብረ ማርያም የ2016 አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ሁሌም እንደሚያደርገው ሁሉ ከ100 በላይ ለሚሆኑ ለሀገራችን ትልቅ ዋጋ ለከፈሉ ለቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የበአል መዋያ ገንዘብ ሰጥተዋል።
ገንዘቡን በመስጠት የተባበሩት ድምፃዊ ካሳሁን እሸቱ፣ ድምጻዊ አዲስ ሙላት ፣ ድምጻዊ ታረቀኝ ሙሉ ሌሎች ድምፃዊያንን በማስተባበር በጋራ በመሆን የበፓስወርድ ላውንጅ ባለቤት ( ፍቅር ኮተትን) ጨምሮ የአንድ ቀን የምሽት ገቢያቸውን በማሰባሰብ ድጋፍ አድርገዋል።
እንዲሁም የህግ ባለሞያ የሆነው ሼክስፒር ፈይሳ ፣ ጃምቦ ትሬዲንግ (አቶ/ሁንዴ )ትሪያ ትሬዲግ ፒኤልሲ እና ሳሙኤል ተሾመ ከቨርጂኒያ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ለቀድሞ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላቶች ድጋፍ አድርገዋል።
595000cookie-checkድምፃውያኖቹ ለቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።no