ሁለት ቤተሰቦችን ያጨቃጨቀዉ ከሞት ተነሳ የተባለዉ ታዳጊ ጉዳይ እልባት አገኘ

Reading Time: < 1 minute

በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ቢለዋንጃ ቀበሌ ከአራት አመት በፊት ሞቶ ተቀብሯል የተባለዉ ታዳጊ ባቂ ሲከማ መሀመድ ጉዳይ እልባት ማግኘቱን ፖሊስ አስታውቋል።

ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከመንገድ ላይ የተገኘው ታዳጊ ከሞት ተነስቶ ነው በማለት የሟች ቤተሰቦች ልጃቸዉ ባቂ ስለመሆኑ አንዳችም የሚያጠራጥር ነገር እንደሌለዉ አረጋግጠዉ ለፈጣሪ የሚሳነዉ ነገር የለም ከሞተ ተነስቶ ህያዉ አድርጎታል ሲሉ ታዳጊዉን ተቀብለው እንደወትሮዉ መንከባከብ መጀመራቸዉ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮና ቲቪ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ ታዳጊ ጋር ሁለንተናዊ መመሳሰል ያለዉ  አብዲ ሄራቶ አቦዬ የሚባል ልጅ ጠፍቶብናል የሚሉ  ቤተሰቦች ከሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ አከባቢ ልጃችን ነው ይሰጠን ሲሉ የመጡ ሲሆን በሁለቱ ቤተሰቦች መካከል የይገባኛል ጥያቄ  መነሳቱም ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወሳል።

አሁን የሁለቱ ቤተሰቦች የይገባኛል ክርክር መቋጫ ማግኘቱ የሁልባረግ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ ዐቃቤህግና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ባደረጉት ማጣራት አብዲ ሄራቶ የሚባል ልጅ ጠፍቶብናል የሚሉ ቤተሰቦች መሆኑ የሚያሳይ በእጅና በእግሩ የተነገሩ  ልዩ ምልክቶችን መኖራቸዉ በማረጋገጥ ታዳጊዉ ጠፍቶብናል ለሚሉ ቤተሰቦች ተላልፎ መሰጠቱ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ተናግረዋል።

ስለዚህ ከአራት አመት በፊት ሞቶ የተቀበረዉ ታዳጊ ከሞት አለመነሳቱ ህብረተሰቡ እንዲያዉቀዉ ሲል ፖሊስ አሳስቧል።

#ዳጉ_ጆርናል
59440cookie-checkሁለት ቤተሰቦችን ያጨቃጨቀዉ ከሞት ተነሳ የተባለዉ ታዳጊ ጉዳይ እልባት አገኘ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE