ኤግል ኮሌጅ በመጀመሪያ  ድግሪ ፕሮግራምያስተማራቸውን  405 ተማሪዎች  ነገ ያስመርቃል

Reading Time: < 1 minute

ኤግል ኮሌጅ በመጀመሪያ ድግሪ መርሃግብር ያስተማራቸውን 405 ተማሪዎች፣ ነገ ጳጉሜ 4 ቀን 2015ዓ.ም በኦሮሚያ ባህል አዳራሽ እንደሚያስመርቅ አስታውቋል፡፡

የምርቃት ሥነስርዓቱ ከከፍተኛ የመንግሥት ተቋማት የተጋበዙ የክብር እንግዶችና የተመራቂ ወላጆች በተገኙበት እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡

ኤግል ኮሌጅ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መርሃግብሮች አሰልጥኖ ሲያስመርቅ የዘንድሮው ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

ኮሌጁ ከኢፌዲሪ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ባገኘው ዕውቅና መሰረት፣ ከመማር ማስተማር በተጨማሪ በጥናትና ምርምር ሥራዎች ላይ በንቃት የሚሳተፍ ሲሆን፤በማህበረሰብ አገልግሎት በዙሪያው ላሉ የመንግሥትና የግል ተቋማት የማህበረሰብ ተኮር ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት፣ ማህበረሰባዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡
59420cookie-checkኤግል ኮሌጅ በመጀመሪያ  ድግሪ ፕሮግራምያስተማራቸውን  405 ተማሪዎች  ነገ ያስመርቃል

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE