በ126 ማህበራት አማካኝነት ማህበረሰቡን ማዕከል ያደረጉ የልማት ድርጅቶች እንዲፈጠሩ እየሰራ እንደሆነ ዴቨሎፕመንት ኤክስፐርቲስ ሴንተር ገለፀ::
ዴቨሎፕመንት ኤክስፐርቲስ ሴንተር ከራስ አገዝ ጥምረትና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን የሰራቸውን ስራዎች ለማሳየትና በበጎ አድራጎት ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ አካላትን ለማስተባበር ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል የመጡ የበጎ አድራጎት ማህበራት ስራዎቻቸውን አሳይተዋል፡፡
ተቋሙ ይበልጥ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ ያለው በራስ አገዝ የተደራጁ ሴቶችና አርሶ አደሩ ማህበረሰብ ላይ እንደሆነ ነው የገለፀው::
በጎ አድራጎትን ከእርዳታ ባሻገር ኅብረተሰቡ ባለው ሃብት የሚሰሩ ስራዎች ላይ ተሳትፎ አድርጎ የልማት አካል እንዲሆን ማስቻል ላይ እንደሚሰራ የዴቨሎፕመንት ኤክስፐርቲስ ሴንተር የፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳንኤል አስፋው ተናግረዋል::
የልማት ድርጅቶች በሚሰሩት ስራ ላይ ማህበረሰቡ በበጎነት ያለውን ሃብትና ጉልበት በመስጠት እንዲሳተፍ ብሎም ድርጅቶች ደግሞ ለማኅበረሰቡ የሚጠቅሙ ስራዎች እንዲሰሩ ለማስቻል እንቅስቃሴዎች እያደረገ እንደሆነም አስታውቋል::
አራዳ ኤፍኤም