በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተለያዩ ታላላቅ ሽልማቶችን ያገኘው እና በአለማቀፍ መድረኮች ዝናን ያተረፈው በኢትዮጵያዊው ወጣት አዚዝ ኡስማን አማካኝነት የተመሠረተው ካሪቡ ግሩፕ መመሠረቱን ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 18 ቀን 2015 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው ማዶ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ይፋ ተደረገ።
ወጣት አዚዝ ኡስማን በአሁኑ ወቅት ደግሞ፣ ያካበተውን እውቀት፣ ልምድና ዝናውን በመጠቀም ተቀማጭነቱን ዱባይ ውስጥ ያደረገ እና የአገሩን ኢትዮጵያን ቱሪዝም ለማሳደግ እና የውጭ ኢንቨስተሮችን ወደ አገሪቱ ለመሳብ የሚሰራ ካሪቡ ግሩፕ የሚባል ድርጅት አቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ከካሪቡ ግሩፕ አላማዎች መካከል ኢትዮጵያዊ የሆኑ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ስመጥር እንዲሆኑ ማስቻል፤ የኢትዮጵያን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ማሳደግ እንዲሁም የአገሪቱን ባለሃብቶች በዓለም ዓቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ለማድረግ በግል ከሚደረጉ ጥረቶች ባለፈ በተቋም ደረጃ ስራዎችን መስራት
እንደሚሰራ የካሪቡ ግሩፕ መስራች ወጣት አዚዝ ኡስማን በመግለጫው ተገልጿል።
ኤግል ኤቨንት ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባሰናዳው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ተከታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
592000cookie-checkኢትዮጵያን ለሌላው አለም የሚያስተዋውቅ ካሪቡ ግሩፕ መመሠረቱን ይፋ ተደረገ።no