አክሽን ፎር ዘ ኔዲ ኢን ኢትዮጵያ ከኢጋድ ጋር በመተባበር በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል ድንበር ሞያሌ አካባቢ ለ34 ወራት የሚቆይ እና በጀርመን ልማት ባንክ በተገኘ የ3.8 ሚሊዮን ዩሮ ኘሮጀክት የሚተገበሩ የንጽሁ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የመንገድ ሥራ ፣ የሞተር ሳይክል ማህበራት ግንባታ ፣የእንስሳት ገበያ ማደስ ተቋም ግንባታ፣የሞተር ሳይክል መጠለያ ግንባታ ሌሎችም የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ኘሮጀክቶች ይፋ ተደርገዋል።
በኬንያና በኢትዮጵያ ድንበሮች መሃል የሚገኙ ስደተኞችን ጨምሮ ለአደጋና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰቦችን ለመርዳት የሚያስችለው ይሄ የፕሮጀክት ስምምነት፣ ነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ነው የተፈረመው ፤ስምምነቱን ኢጋድን በመወከል የኢጋድ ዋና ጸሃፊ የተከበሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የፈረሙ ሲሆን፤ አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያን በመወከል ደግሞ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ አቶ ሳሊሁ ሱልጣን እንደፈረሙ ታውቋል፡፡
ፕሮጀክቱ ችግረኞችን ከመርዳት ባሻገር በኢትዮጵያ ሞያሌና በኬንያ ሞያሌ ድንበሮች የሚገኙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮችን ለማጠናከር እንደሚረዳ ታምኖበታል ተብሏል፡፡
በ2022 የበጀት ዓመት የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፍ ሥራዎችን ማከናወኑን የጠቆመው አክሽን ፎር ዘ ኒዲ፤ በዚሁ ወቅት 1.3 ቢሊዮን ብር በሥራ ላይ ማዋሉንና ከዚህ ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የገንዘብ ድጋፍ ያገኘው ከዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ (UNHCR) መሆኑን አመልክቷል፡፡
አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢን ኢትዮጵያ፤ በ2004 ዓ.ም በጥቂት ለጋሾችና በጎ አድራጊዎች የተመሰረተ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ 11 ቅርንጫፍ ቢሮዎችን በመክፈትና ከ700 በላይ ቋሚና ብቁ የሆኑ ከፍተኛ ባለሙያዎችን በመቅጠር በሁሉም ክልሎች ሰብአዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡
591800cookie-checkለ34 ወራት የሚቆይ የ3.8 ሚሊዮን ዩሮ ኘሮጀክት ይፋ ተደረገ።no
በኬንያና በኢትዮጵያ ድንበሮች መሃል የሚገኙ ስደተኞችን ጨምሮ ለአደጋና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰቦችን ለመርዳት የሚያስችለው ይሄ የፕሮጀክት ስምምነት፣ ነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ነው የተፈረመው ፤ስምምነቱን ኢጋድን በመወከል የኢጋድ ዋና ጸሃፊ የተከበሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የፈረሙ ሲሆን፤ አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያን በመወከል ደግሞ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ አቶ ሳሊሁ ሱልጣን እንደፈረሙ ታውቋል፡፡
ፕሮጀክቱ ችግረኞችን ከመርዳት ባሻገር በኢትዮጵያ ሞያሌና በኬንያ ሞያሌ ድንበሮች የሚገኙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮችን ለማጠናከር እንደሚረዳ ታምኖበታል ተብሏል፡፡
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢን ኢትዮጵያ፤ በ2004 ዓ.ም በጥቂት ለጋሾችና በጎ አድራጊዎች የተመሰረተ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ 11 ቅርንጫፍ ቢሮዎችን በመክፈትና ከ700 በላይ ቋሚና ብቁ የሆኑ ከፍተኛ ባለሙያዎችን በመቅጠር በሁሉም ክልሎች ሰብአዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ