ለበጎ አድራጎት የሚውል የሃያ ሚሊዮን ብር ኘሮጀክት ይፋ ሆነ።

Reading Time: 2 minutes
ለችግር የተዳረጉ ወላጅ ያጡ ጨቅላ ህጻናትን ከአስከፊ ህይወት ለመታደግ ያለመ የሀያ ሚሊዮን ብር ኘሮጀክት ዛሬ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በዮድ አቢሲኒያ ኢንተርናሽናል ሆቴል የኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት መርሐግብር ይፋ ሆነ።

ዛሬ በተከናወነው መርሐግብር ላይ ይፋ ከተደረገው ኘሮጀክት ባሻገር ድምጻዊ ማትያስ ተፈራ እና አርቲስት ማርታ ግርማ የቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት የክብር አምባሳደር ሆነው ተሽመዋል።

የቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ገነት ገብረ ማርያም በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብሩ ላይ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ድርጅታቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ቢሮ ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት 15 በተለያየ ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትን ተረክበው በማሳደግ እንዲሁም ለችግር የተጋለጡ 30 እናቶች 46 ህፃናት ያሏቸው በየወሩ የምግብ፤ የጽዳት የአልባሳትና የሕክምና ድጋፍ እያደረግን እንገኛለን ያሉት ወይዘሮ ገነት ገብረ ማርያም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በቻለው አቅም የአንድ ሕፃን ሕይወት ተስፋ ለማለምለም ከቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጎን እንዲቆሙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በተለያዩ ምክንያት ለችግር የተዳረጉ ወላጅ ያጡ ጨቅላ ህጻናትን ከአስከፊ ህይወት ተላቀው መሠረታዊ ፍላጎታቸው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተሟልቶላቸው ከማኅበረሰቡ ዘሌቀታዊ አገልግሎት ሲያገኙ እና የተቸገሩ እናቶች (ሴቶች) ወደ ጎዳና እንዳይወጡ ድጋፍ በማድረግ ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው በመልካም ህይወት ሲኖሩ ማየትን ራዕዩ አድርጎ የተመሠረተው የቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት
ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እጅግ በጣም ብዙ ለአርአያነት የሚጠቀሱ ለሀገር እና ለወገን የሚጠቅሙ ስራዎችን የሰራ ሲሆን በተለይ አሁን ላይ በአዲስ አበባ እና በመላው የሃገሪቱ ክፍሎች በርካታ እናቶች በተለያዩ ምክንያቶች ህጻናት ልጆችን ይዘው ለልመና ጎዳና ላይ በመውጣት ለተለያዩ እንግልቶች እና ስቃዮች በመጋለጥ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ይህን ከባድ ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ በከፍተኛ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።

ድርጅቱ እናቶችን እና ህጻናቱን በቋሚነት ለመደገፍ ሃያ ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ የዳቦ ቤትና መሰል የምግብ ማቀነባበሪያ ፕሮጀክት ቀርጾ ወደ ስራ በመግባት ላይ ሲገኝ
ቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለማገዝ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥር 1000334287169 ላይ መርዳት ትችላላችሁ።

(ጌች ሐበሻ)
???? Moges Mekonnenn

58940cookie-checkለበጎ አድራጎት የሚውል የሃያ ሚሊዮን ብር ኘሮጀክት ይፋ ሆነ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE