በፈጠራ ባለሙያው በአቶ ጎይቶኦም ገብረ ዮሐንስ ይፋ የተደረገው ፈጠራ በተሸከርካሪ መኪኖች ላይ የሚገጠም አውቶማቲክ አደጋ ጠቋሚ መሳሪያ ተሰርቶ ዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች እና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በተገኙበት በሀርመኒ ሆቴል ይፋ ሆነ።
በከተማችን እንዲሁም በሀገራችን እየደረሰ ያለውን የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከል እንዲያስችል አቶ ጎይቶኦም ገ/ዮሐንስ በተባሉ አንድ የፈጠራ ባለሙያ በተሸከርካሪ መኪኖች ላይ የሚገጠም አውቶማቲክ አደጋ ጠቋሚ መሳሪያ የተሰራ ሲሆን ይህም በአእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን ፓተንት ያገኘና ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ብሎም ከአጋር ተቋማትም የድጋፍ ደብዳቤና እውቅናን አግኝቷል።
በተለምዶ አንድ አሽከርካሪ እያሽከረከረ ሲሄድ ከፊት ለፊቱ ከቀኝ ወደ ግራ የሚያቋርጡ እግረኞች ተሽከርካሪዎች ወይም እንስሳት ሲያጋጥሙ የተሽከርካሪን ፍጥነት ቀንሶ በመቆም በግራ እስፖኪዮ ሲመለከት በሱ ግራ በኩል ደርቦ የሚመጣ ተሽከርካሪ ሲያይ ግራ እጁን አውጥቶ በማወዛወዝ በግራ በኩል ደርቦ ለመጣው አሽከርካሪ ፍጥነቱን እንዲቀንስ ብሎም እንዲቆም በማድረግ ከቆመው ተሽከርካሪ ፊት በኩል በሚሻገሩት እግረኞችም ሆነ ተሽከርካሪዎች ላይ አደጋ እንዳያደርስ ይደረጋል፡፡ ይሄም በመደረጉ ብዙ አደጋዎችን መከላከል አስችሏል፡፡
ግን በተቃራኒ በኩል እግረኞችም ሆነ ተሽከርካሪዎች ከግራ ወደ ቀኝ በሚቋርጡበት ጊዜ በቆመው ተሽከርካሪ ቀኝ ጐን ደርቦ ለሚመጣው አሽከርካሪ ግን ምልክት መስጠት ስለማይቻል ከ80% በላይ በእግረኞች ላይ የሚደርሰው አደጋ ከፍተኛ ድርሻው በቀኝ ጐን ደርቦ በሚመጣ አሽከርካሪ በሚደርሰው አደጋ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ልክ እንደ ግራ እጃችን ቀኝ እጃችንን አውጥተን ምልክት ለመስጠት ስለሚያዳግተን እንደ አማራጭ የምንጠቀመው ሀዛርድ ማብራት ወይም ቀኝ ፍሬቻን ማብራት ነው፡፡ ሆኖም ግን እነዚህን በመጠቀማችን በእጃችን የምንሰጠውን ያህል አያግዝም፡፡
እነዚህን ችግሮች ትርጉም ባለው ሁኔታ ይፈታል የተባለው ይህ የፈጠራ ሥራ ውስብስብ ያልሆነና በቀላሉ የሚተገበር የፈጠራ ሥራ መሆኑን የፈጠራው ባለሙያ የሆኑት አቶ ጎይቶም ገ/ዮሐንስ የገለፁ ሲሆን ይህም ግራና ቀኝ ጐን እንዲገጠም ተደርጎ የተሰራ እና ከዳሽ ቦርድ በተዘጋጀለት ቦታ ላይ ኦን ስናደርገው እንደየተሽከርካሪው የፊት አቀማመጥ አውቶሞቢሎች ላይ ከቀኝ ጎን ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ከጋቢና ጀርባ ውበቱን በጠበቀ መልኩ የሚገጠም እና ከዳሽ ቦርድ ኦን ሲደረግ በውጭ ጎን ውበቱን ጠብቆ የተገጠመው እስቶፕ ጹሁፍ ያለው የእጅ ምልክት የያዘ እና መብራት እና ለሌት እንዲያግዝ አንጸባራቂ ያለው የቁም ምልክት ውዝዋዜን በመፍጠር በእኛ ቀኝ በኩል ደርቦ ለሚመጣው አሽከርካሪ ግልጽ ምልክት በመስጠት ከኔ ፊት የሚሻገሩ እግረኞችም ወይም ተሽከርካሪዎች ብሎም እንስሳቶች ስላሉ ፍጥነትን ቀንስ ከዛ አልፎም ቁም በማለት አደጋ እንዳይደርስ የሚያደርግ ዲቫይስ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡
589200cookie-checkበተሽከርካሪ ተከልሎ ማለፍ የሚደርስን አደጋ የሚከላከል የፈጠራ ስራ ይፋ ሆነ።no