የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር የምስረታ ጉባኤውን አካሄደ።

Reading Time: < 1 minute
የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር ዛሬ ነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በሀይሌ ግራንድ አዲስ አበባ ሆቴል በዛሬው እለት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የኪነጥበብ እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በተገኙበት አካሂዳል።

ከምስረታ ጉባኤው ቀደም ብሎ የማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አሸናፊ ሙሉጌታ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫው እንደገለጹት ማህበሩ መመስረቱ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ሲሆን በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች እንዲሰባሰቡ፣ ሀሳብ እንዲለዋወጡና ለኢንዱስትሪው ዕድገት በጋራ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ወሳኝ መድረክ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

ማህበሩ በኢትዮጵያ በሚገኙ ትላልቅ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ብራንድ ባላቸው ሆቴሎችና የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ውስጥ በርካታ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች የተቋቋመ የሙያ ማህበር ሲሆን አዲስ አበባ በአለም ላይ ከኒውዮርክና ከጁኔሻ በመቀጠል ሶስተኛዋ የበርካታ ዲኘሎማቶች መቀመጫ እንድመሆኗ መጠን በከተማዎ ያለውን የሆቴልና ቱሪዝም የአገልግሎት አሰጣጥ የከተማዋን ስም አና ደረጃ በሚመጥን መልኩ እንዲሆን በዋናነት በሙያው እና ሙያተኞች ልህቀት እና ሙያዊ ከህሎት ላይ ራዕይ ይዞ የሚስራ ሲሆን ይህም የከተማዎን ገፅታ በማስድግ ሌሎች የቱሪስት መዳረሻዎች ምቹ ሁኔታን እንደ ሚፍጥር በማመን ነው ማህበሩ በዘርፉ በጥናትና ምርምር፤ በስልጠናና በማነነር ሙያዊ አበርክቶን ለመወጣት እቅድ ይዞ የተነሳ መሆኑን በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

(ጌች ሐበሻ)

58900cookie-checkየአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር የምስረታ ጉባኤውን አካሄደ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE