የአሜሪካኑ ፕሮፌሽናል ቢዩቲ አሶሲየሽን (PBA) አባል የሆነው ጆርዳን የውበት አካዳሚ በሜካፕ ፣ በጥፍር ማስዋብ ፣ በፊት ቆዳ አጠባበቅ ፣በአይን ሽፋሽፍት ፣በቅንድብ ሂና እንዲሁም በዋክስ ስልጠና በንድፈ ሐሳብ እና በተግባር ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን 120 ሰልጣኞችን ትናንት ነሐሴ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ቦሌ አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው ሁለተኛው እና በአዱሱ የማሰልጠኛ ተቋም ላይ አስመረቀ።
የጆርዳን የስነ-ውበት ማሰልጠኛ ተቋም መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እስራኤል ብርሃኑ በተለይ ለየኔቫይብ ዝግጅት ክፍል እንደገለጹት “ስለ እሷ ያገባኛል” የሚለውን ኘሮጀክት ጋር በቅንጅት በተለያየ ምክንያት መክፈል ያልቻሉ ሰልጣኞችን ከዳሽን ባንክ እና ከቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በተደረሠ ስምምነት መሠረት በረጅም ጊዜ በሚከፈል ክፍያ ሰልጥነው የሚሰሩበትን ፤ እየሰሩ የሚከፍሉበትን እድል ከማመቻቸት ባሻገር ምንም አይነት አቅም የሌላቸውን ሴቶች ደግሞ ስፖንሰር በማፈላለግ የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ ማኀበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ” እንደሆነ ገልጸውልናል።
ተመራቂ ሰልጣኞችን ከስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ጋር በመተባበር በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የስራ እድል እያመቻቸን ነው ያሉት አቶ እስራኤል በቀጣይ ጆርዳን የስነ-ውበት ማሰልጠኛ ተቋም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ተጨማሪ የማሰልጠኛ ተቋማትን በመክፈት በሙያው የሰለጠኑ እና ብቁ የውበት ባለሙያዎችን ለመፍጠር በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በስልጠና ወቅት የማሰልጠኛ ተቋሙ አመራሮች እና መምህራኖቻችን ብቁ ሁነን እንድንወጣ ሙያዊ ድጋፍ አድርገውልናል ያለችው የሜካኘ ተመራቂዋ ሜላት ፍትዊ በነበረን ሶስት ወር ቆይታ ስለ ስነውበት በክፍል ውስጥ እና በተግባር ያገኘነው ስልጠና እንደጠቀማት እና በአለም አቀፍ ደረጃ በሰለጠንበት ሙያ ዘርፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችለናለች ብላለች።
በመርሐግብሩ ላይ ተመራቂዎች የተመራቂ ቤተሰቦች ፣ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ፣ የኪነጥበብ እና የመገገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ተገኝተዋል። ጆርዳን የስነ-ውበት ማሰልጠኛ ተቋም ቦሌ አደይ አበባ ስታዲየም መብራቱ ጋር ካለው በተጨማሪ በመገናኛ ቤተልሔም ኘላዛ ላይ የስነ ውበት ተማሪዎችን ተቀብሎ በማሰልጠን ላይ ይገኛል።
(ጌች ሐበሻ)
588600cookie-checkጆርዳን የስነ-ውበት ማሰልጠኛ ተቋም ለስድስተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።no
የጆርዳን የስነ-ውበት ማሰልጠኛ ተቋም መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እስራኤል ብርሃኑ በተለይ ለየኔቫይብ ዝግጅት ክፍል እንደገለጹት “ስለ እሷ ያገባኛል” የሚለውን ኘሮጀክት ጋር በቅንጅት በተለያየ ምክንያት መክፈል ያልቻሉ ሰልጣኞችን ከዳሽን ባንክ እና ከቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በተደረሠ ስምምነት መሠረት በረጅም ጊዜ በሚከፈል ክፍያ ሰልጥነው የሚሰሩበትን ፤ እየሰሩ የሚከፍሉበትን እድል ከማመቻቸት ባሻገር ምንም አይነት አቅም የሌላቸውን ሴቶች ደግሞ ስፖንሰር በማፈላለግ የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ ማኀበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ” እንደሆነ ገልጸውልናል።
ተመራቂ ሰልጣኞችን ከስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ጋር በመተባበር በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የስራ እድል እያመቻቸን ነው ያሉት አቶ እስራኤል በቀጣይ ጆርዳን የስነ-ውበት ማሰልጠኛ ተቋም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ተጨማሪ የማሰልጠኛ ተቋማትን በመክፈት በሙያው የሰለጠኑ እና ብቁ የውበት ባለሙያዎችን ለመፍጠር በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
በመርሐግብሩ ላይ ተመራቂዎች የተመራቂ ቤተሰቦች ፣ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ፣ የኪነጥበብ እና የመገገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ተገኝተዋል። ጆርዳን የስነ-ውበት ማሰልጠኛ ተቋም ቦሌ አደይ አበባ ስታዲየም መብራቱ ጋር ካለው በተጨማሪ በመገናኛ ቤተልሔም ኘላዛ ላይ የስነ ውበት ተማሪዎችን ተቀብሎ በማሰልጠን ላይ ይገኛል።
(ጌች ሐበሻ)
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ