ባሮክ ኢቨንት ኦርጋናይዘር መጪውን የ2016 አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው እና ከነሀሴ 20 እስከ ጷግሜ 6 የሚቆይ የንግድ እና የባዛር ትርዒት ለሸማቾች እና ለጎብኝዎች ክፍት ሆኗል።
ባሮክ ኢቨንት ከባዛሩ ባሻገር ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ለአምስት መቶ ሰዎች የማዕድ ማጋራት በማድረግ የማህበራዊ ሀላፊነትን በመወጣት ዝግጀቱን እንደከፈቱ የባሮክ ኢቨንት ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ ገልፀዋል ።
አቶ ሰለሞን አክለውም የዘንድሮው “መርካቶን በሚሊኒየም” ኤክስፖና ባዛር የኑሮ ውድነቱን ባገናዘበ መልኩ ነጋዴው በምክንያታዊነት የሚያተርፍበት ሸማቹ በአቅሙ በእውነተኛ ቅናሽ የሚፈልገውን በአይነት በጥራትና በሰፊ አማራጭ የሚገበያይበት በየእለቱ በሚቀርቡ ደማቅ ኮንሰርቶችና የመዝናኛ ዝግጅቶች ዘና እያሉ ያሻቸውን እየበሉና እየጠጡ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ የሚሣተፍበት በአንድ ድንጋይ ሁለት ብቻ ሣይሆን ከዚያም በላይ ግቦችን የሚመቱበት ይሆናል ብለዋል ።
በርካታ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ አምራቾችን አስመጭና ላኪዎችን ጅምላ አከፋፋይና ችርቻሮ ነጋዴዎች የሚሳተፉበት “መርካቶን በሚሊኒየም ” የተሰኘው ደማቅ የአዲስ አመት ኤክስፖና ባዛር ለነጋዴና ለሸማቹ ብቻ ሣይሆን በበጎ ስራ ላይ ለተሰማሩ ተቋማትም ጭምር ትልቅ እድል ይዞ የመጣ እንደሆነ ተገልጿል።
«መርካቶን በሚሊንየም» በሚል ለቀጣይ ለተከታታይ 17 ቀናት በሚቆየው በዚህ የንግድ አውደ ርዕይ ላይ ከአንድ ሺህ በላይ የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ሀገር ኩባኒያዎች ፣ ሪል-እስቴቶች የፋይናንስ ተቋማት ፣ የምግብ እና የአልባሳት ምርት አቅራቢዎች ፣ የስጦታ እቃዎች ፣ የቤት እና የቢሮ መገልገያ በአጠቃላይ መርካቶ ውስጥ የሚገኙ እቃዎችን በአንድ ላይ የሚገኝበት የንግድ አውደ ርዕይ ሲሆን በቀን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሸማቾች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።
አዘጋጆቹ በመክፈቻው መርሐግብር እንደገለፁት ፤ ይሄ ታላቅ የአውዳመት የንግድ ትርኢት፤ ነጋዴዎች ለሸማቹ እጅግ ቅናሽ በሆነ ዋጋ ጥራት ያላቸው ፍጆታዎችን በሰፊ አማራጭና ዓይነት የሚሸጡበት፣ ሻጭና ገዥ በአንድ ቦታ ላይ የሚገበያዩበት፤ እንዲሁም መሰረታዊና የበዓል ፍጆታዎች በስፋት የሚቀርቡበት ይሆናል ብለዋል፡፡
እስከ አዲስ ዓመት ዋዜማ ለተከታታይ ቀናት የሚዘልቀው የንግድ ኤግዚቢሽንና ባዛሩ፣ ትርፍን ብቻ ታላሚ አድርጎ የተዘጋጀ አይደለም የተባለ ሲሆን፤ ትናንት በይፋ የተከፈተው ባልተለመደ መልኩ 500 ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ማዕድ በማጋራት ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም፣ 15 የሚሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሥራቸውንና ዓላማቸውን ለህብረተሰቡ የሚያስተዋውቁበት ቦታ በዚሁ በሚሊኒየም አዳራሽ በነጻ እንደተሰጣቸው የባዛሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በንግድ ባዛሩ መክፈቻ ላይ በተከናወነው ማዕድ የማጋራት ሥነስርዓት፣ ከተለያዩ የከተማዋ ወረዳዎች ለተውጣጡ 500 ያህል ግለሰቦች ዘይት፣ ዱቄትና እንቁላል የተበረከተላቸው ሲሆን፤ ለዝግጅቱ የወጣውን ወጪ እናት ባንክና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ የንግድ ተቋማት እንደሸፈኑት ተነግሯል፡፡
“መርካቶን በሚሊኒየም” የንግድ ባዛር፣ የተለያዩ ምርቶችና የበዓል ፍጆታዎች ለሽያጭ የሚቀርቡበት ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡ የሚዝናናበትም መድረክ ነው ያሉት አዘጋጆቹ፤ ለዚህም ታዋቂና ተወዳጅ ድምጻውያን በየቀኑ የሚያቀነቅኑበት የሙዚቃ ድግስ እንደሚቀርብ ጠቁመዋል፡፡
587000cookie-check“መርካቶን በሚሊኒየም” የተሰኘ የንግድ እና ባዛር ትርዒት በሚሊየም አዳራሽ ተከፈተ ።no