ሀገር አቀፍ የሂሳብ ትምህርት የፍፃሜ ውድድር በአዲስ አበባ እየተካኸደ ነዉ።

Reading Time: 2 minutes
ማይ ሶርባን ስፔሊንግ ቢ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያሰናዳው የሂሳብ ትምህርት ይከብዳል የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት ለማሰወገድ ።” የሂሳብ ትምህርት ያሸልማል” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ በሚገኙ 10 ከተሞች ሲያካሂድ የቆየው ሀገር አቀፍ የፍጻሜ ውድድር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወነ ይገኛል።

የፍጻሜ ውድድሩ ማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ ተገኝተው ለተማሪዎች እና ለወላጆች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ምክትል ኘሬዝዳንት ዶክተር አብርሃም ደበበ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የሒሳብ ትምህርት ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ
አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የማይ ሶርባን ስፔሊንግ ቢ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መስራች እና ዋና አስተባባሪ መምህር ከበደ አጥናፊ ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት እንገለጹት በ2015 ዓ. ም በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ አስር ከተሞች ማለትም አዲስ አበባ ፣ ሐረር ፣ ድሬዳዋ ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ሐዋሳ ፣ ጎንደር ፣ አዳማ ፣ ቢሾፍቱ ፣ ባህርዳር እና ደብረ ብርሃን ከተሞች ፣ከአራት መቶ በላይ ትምህርት ቤቶች ፣ ከ120 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለወራት የሂሳብ ስሌት ውድድር ሲያደርጉ የቆዮ ሲሆን በአምስት ዙር ሲካሄድ የቆየው ውድድር 965 ተማሪዎችን ወደ ፍፃሜ ፉክክር በማድረስ ከዛሬ ነሀሴ 19 እስከ ፊታችን እሁድ ነሐሴ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወነ እንደሚቆይ ገልጸዋል።

ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የተማሪዎች የሒሳብ ውድድር ከ3ኛ ክፍል እስከ 12 ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በአማርኛ ፣በእንግሊዝኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በወላይተኛ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ የቀረበላቸውን የቅድመ ማጣሪያ የጽሁፍ ፈተና ያለፉ ተማሪዎች በመድረክ ላይ በሚኖረው የቃል የሒሳብ ፈተና ለፍጻሜ ውድድር እንደሚቀርብ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

በዚህ በሚከናወነው የፍፃሜ ውድድር ላይ ከየከተሞቹ ለመጡ ተወዳዳሪ አሸናፊዎች የዋንጫ ፣ የሜዳሊያ ፣ የሰርተፍኬት እንዲሁም የገንዘብ ሽልማት በክፍል ደረጃቸው ተሸላሚ ይሆናሉ።

58660cookie-checkሀገር አቀፍ የሂሳብ ትምህርት የፍፃሜ ውድድር በአዲስ አበባ እየተካኸደ ነዉ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE