አሸዋ ቴከኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ልዩ የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አስታወቀ።

Reading Time: 2 minutes
አሸዋ ቴከኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ከነገ ነሃሴ 20 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ህዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ የአክሲዮን ሽያጭና ልዩ የኢንቨስትመንት ጥቅም የሚያስገኝ እድል መጀመሩን ትናንት ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴልበተሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

አሸዋ ቴከኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ በአሁኑ ሰአት መሰረቱን በጠንካራ አለት ላይ የጣለ 10 የቦርድ አባላቶች ያሉት፣ ከ1500 በላይ ባለ አክሲዮኖች ያሉት፤ 200 በላይ የበቁ ባለሙያዎችን ይዞ ቅርንጫፉን በኬንያ ከፍቶ በመቶ ሺህ ተጠቃሚዎችን አፍርቶ፣ ብዙ ሶሉሽኖችን አፍርቶ፣ ፍቃድ ወስዶ በጣም ትልቅ ስራን እየሰራ ያለ ተቋም እንደሆነ በመግለጫው ተገልጿል ።

ድርጅቱ ሲቋቋም ከሚያስፈልገው 200 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ወደ 2 ቢሊየን ብር ከፍ እንዲል ቦርዱ በወሰነዉ መሰረት ቀሪ አክሲዮኖችን በአጭር ጊዜ ሸጦ ለመጨረስ የተለያዩ ፓኬጆችን በማዉጣት እየሰራ ነው። በዛሬዉ እለትም ”ስማርት ሶሉዩሽን ለስማርት ኢንቨስተሮች ” በሚል ትልቅ ራዕይ በመሰነቅ በስኬት ጎዳና ላይ እየተጓዘ እንደሚገኝ ነው የተነገረው።

ይህንን አላማ ከግብ ለማድረስ ለኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች ልዩ የኢንቨስትመንት ጥቅም የሚያስገኝ እድል ይዞ የመጣ ሲሆን በተለይም ምርት እና መፍትሄዎቹን በተመለከተ የአሽዋ ስማርት (ERP) የሰው ሀብት አስተዳደር የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ኢንዱስትሪ እና የመሳሰሉትን የቢዝነስ ክንውኖችን የሚያቀላጥፍ የተቋማትን ወጭ የሚቀንስ ትርፋማነትን የሚጨምር፣ ቀልጣፋ የአሰራር ሂደትን የሚፈጥር ሁሉንም በአንድ ላይ የያዘ ከ13 በላይ ኢንዱስትሪዎችን የሚሸፍን ምቹ ፣ ቀላል፤ አስተማማኝ የሆነ ሶፍትዌር በሳስ እና በሽያጭ መልክ ለገበያ አቅርቧል።

ሌላኛዉ Smart Website Bulgn የኛ ድረ ገጽ መገንቢያ በደቂቃዎች ውስጥ ድንቅ ድረ-ገጾችን እንዲፈጥሩ ይፈቅድልዎታል። እንዲሁም በደንበኞች ላይ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሶፍትዌር/custom software/- ለፍላጎትዎ የተዘጋጁ ሞባይል አፕ እና ዌብ ሳይት ግንባታ በማቅረብ የእርስዎን የንግድ ሃሳቦች ወደ ትርፋማ ንግድ እንዲቀይሩ ያግዛል።

አንድ ባለ አክሲዮን በ500ሺ ብር ሲገባ በአጠቃላይ በድምሩ 6,910,762 25 የሚያገኝ ሲሆን ከ4 አመት በኃላ መደበኛ ባለ አክሲዎን በመሆን የጠቅላላ ትርፍ ተካፋይ ይሆናል የተባለ ሲሆን አንድ ዩኒት 20 አክሲዮን ሲሆን የአንዱ አክሲዮን ዋጋ 500 ብር ነዉ፡፡ አንድ ሰው የሚገዛው ዝቅተኛው ድርሻ 200 አክሲዮን ወይም ከ 500.000 ብር ጀምሮ ሲሆን አንድ ሰው የሚገዛው ከፍተኛው ድርሻ 40,000 አክሲዮን ወይም 200 ዩኒት 100 ሚሊዮን ይሆናል፡፡

ቅድሚያ ክፍያ 50% ጀምሮ ቀሪውን ውል በገቡ በአንድ አመት ውስጥ ይከፍላሉ ተብሏል

58620cookie-checkአሸዋ ቴከኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ልዩ የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አስታወቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE