ግእዝ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ ላይ መሆኑን ገለጸ።

Reading Time: 2 minutes
በምስረታ ላይ የሚገኘው ግእዝ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ መደበኛውን ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የባንኩ አደራጆች ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2015ዓ.ም ለአክሲዮን ገዢዎች ፣ ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በተገኙበት መድረክ ላይ አሳውቀዋል።

ግዕዝ ባንክ አ.ማ የአክሲዮን ሺያጭ ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለምስረታ ሂደት የሚያበቃው የአክሲዮን ሽያጭ ማከናወን መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን በኢትዮጵያ ያለፉት ሶስት አመታት በተፈጠረው የኮቪድ ወረርሽኝ እና በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው የሰላም እጦት ምክንያት የባንኩ እንቅስቃሴ ተገቶ መቆየቱን የባንኩ አደራጆች ገልጸው ፤ አሁን ላይ በአገራችን ያለውን የሰላምና መረጋጋት ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከባለ ድርሻ አካላት ጋርም በቅርበት በመነጋገርና በማደራጀት ዳግም የአክሲዮን ሽያጭ ከተጀመረ ጀምሮ ከ13,800 በላይ የአክሲዮን ገዢዎች መካከል 1.8 ቢልዮን የተፈረመ ፣ ከ850 ሚሊዮን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል እንዲሁም በውጭ አገሮች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አክሲዮን ለመሸጥ በተከፈተ ስዊፍት ኮድ አካውንት አማካኝነት 1.45 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰብ መቻሉን በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

ለሽያጭ የቀረቡ የግዕዝ ባንክ የአክስዮኖች ብዛት 5 ሚልየን ዕጣዎች ሲሆኑ ጠቅላላ ዋጋቸውም ብር 5 ቢልየን ነው። የባንኩ መስራች ለመሆን ዝቅተኛ የአክስዮን ብዛት 100 አክሲዮን ማለትም ብር 100,000 ሲሆን ከፍተኛ ደግሞ 250 ሺህ አክሲዮን ወይም ብር 250 ሚልዮን ነው፡፡

ዘመናዊ አሰራር እና ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከኢትዮጵያ አልፎ በምስራቅ አፍሪካ በደንበኞቹ ተመራጭ የሆነ ባንክ ለመመስረት በዝግጅት ላይ የሚገኘው ግዕዝ ባንክ አክስዮኖች በሁሉም ባንኮች በመሸጥ ላይ ሲሆን 25 በመቶውን ብቻ ቅድምያ በመክፈል የመስራች አክስዮን መግዛት እንደሚቻል የባንኩ አደራጆች ገልጸዋል።

ግእዝ ባንክ አክስዮን ማኀበር በኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/6/2003 እና አዋጅ ቁጥር 592-2008 መሰረት አስፈላጊውን ህጋዊ ደንብ እና መመሪያዎችን ተከትሎ በመስራት ላይ ይገኛል።

58340cookie-checkግእዝ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ ላይ መሆኑን ገለጸ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE