በመዲናዋ የምትገኙ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች በሙሉ ከነገ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ከአሽከርካሪው ውጪ ሌላ ተጨማሪ ተሳፋሪ ሳይጨምሩ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደሚቻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል፡፡
ከተፈቀደው የሰው መጫን አቅም በላይ በሚጭኑ ማህበራትና አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም እየገለፀ፤ አሽከርካሪዎችም ለትራፊክ አደጋ መንስኤ ከሆኑ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር፣ የራስ ቆብ መከለያ (ሄልሜት) አለመጠቀም፣ ከወንጀል ድርጊት በመራቅና ወንጀል የሚፈጽሙ ሲያጋጥሙም ለጸጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ ቢሮው ያሳስባል፡፡
FastMereja