“እንቁጣጣሽ ” የአዲስ አመት የንግድ አውደ ርዕይ ተከፈተ

Reading Time: 2 minutes
ሴንቸሪ ኘሮሞሽንና ኢቨንትስ ያሰናዳው “እንቁጣጣሽ ” የአዲስ አመት የንግድ አውደ ርዕይ እና ባዛር ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ ተከፈተ።

ከ500 በላይ የንግድ ተቋማት እና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጎቢኚዎች የሚሳተፉበት የንግድ አውደ ርዕይ ላይ በየዕለቱ ዝነኛ አርቲስቶች የሚሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት እንደተዘጋጀ የሴንቸሪ ኘሮሞሽንና ኢቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘውግ ጀማነህ በማስጀመሪያ መርሐግብሩ ላይ ገልጸዋል።

“እንቁጣጣሽ” በሚል መጠሪያ ያለው የንግድ አውደ ርዕይ እና ባዛር ከዛሬ ነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ እስከ አዲስ አመት ዋዜሜ ጳጉሜ 6 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ለ24 ቀናት ለሸማቾች እና ለጎብኝዎች ክፍት ሁኖ እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ በመክፈቻው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።

ሴንቸሪ ኘሮሞሽንና ኤቨንትስ በ 1991 ዓ.ም የተቋቋመ የማስታወቂያና የፕሮሞሽን ድርጅት ሲሆን ተቋሙ በመጪው ዓመት የተመሠረተበትን 25ኛ የብር ኢዩቤልዩ በዓሉን ያከብራል።

( ጌች ሐበሻ)

58140cookie-check“እንቁጣጣሽ ” የአዲስ አመት የንግድ አውደ ርዕይ ተከፈተ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE