በ10 ዓመት ውስጥ ለ100 ሺሕ የመኖሪያ ቤቶች ለመገንባት የሚያስችል የቤት ኘሮጀክት ይፋ ሆነ።

Reading Time: 2 minutes
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች በ77 ሺሕ 280 ብር ቅድመ ቁጠባ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ሞዴል ፕሮጀክት ዛሬ ነሐሴ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ አድርጓል።

ድርጅቱ ያስተዋወቀው ፕሮጀክት “Key Common Housing Fund (Key-CHF) የተሰኘ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያለውን ቤት ፈላጊ ማህበረሰብ ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግሩም ይልማ ገልጸዋል።

ድርጅቱ አሁን ላይ የጀመረው የቤት ሞዴል፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያለውን ቤት ፈላጊ ማህበረሰብ ታሳቢ በማድረግ የተጀመረ መሆኑ የገለጸ ሲሆን አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ በቀላሉ እና “በተዘዋዋሪ የቁጠባ ፈንድ “ሞዴል በባለቤትነት የሚረከቡበትን ቤት ክፍያ ይፈፅማሉ ተብሏል።

ይህ ክፍያ የሚፈፀው በዳሽን ባንክ የዝግ አካውንት ሲሆን፣ ድርጅቱ በተጨማሪም የቤት ክፍያ ሞዴልን ተአማኒነት ከፍ ለማድረግ ከቡና ኢንሹራንስ ጋር እየሰራ መሆኑንም ተናግሯል።

በዚህም መሠረት ቤት ፈላጊዎች በ77 ሺሕ 280 ብር የመጀመሪያ ክፍያ እና ከ2 ሺሕ ብር ጀምሮ በሚደረግ እና ለ30 ዓመት በሚዘልቅ ወርሀዊ ቁጠባ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት መንገድ መመቻቸቱን የገለጹት ግሩም፤ በተጨማሪም ለአምስት ዓመት ኢንሹራንስ 2 ሺሕ 672 ብር መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

የቤት ዕድሉ በባለ አንድ፣ ባለኹለት እንዲሁም በባለሦስት መኝታ ቤቶች የተዘጋጀ ሲሆን፤ ተመዝጋቢዎች ቤቱ እስኪደርሳቸው ድረስ ለባለ አንድ መኝታ 2 ሺሕ 230 ብር፣ ለባለ ኹለት መኝታ 2 ሺሕ 730 ብር እንዲሁም ለሦስት መኝታ 3 ሺሕ 730 ብር በየወሩ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል ተብሏል።

በተጨማሪም ቤቶቹ ተገንብተው ካለቁ በኋላ ዕጣ የወጣላቸው ባለዕድለኞ፤ ለባለ አንድ መኝታ 300 ሺሕ ብር የሚከፍሉ ሲሆን፤ ለባለ ኹለት እና ባለሦስት መኝታ ደግሞ 550 ሺሕ ብር እና 800 ሺሕ ብር መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል።

ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን በቤት ልማት፣ ተዘዋዋሪ የቁጠባ ፈንድ፣ በአይቲ እና ማርኬቲንግ መስኮች በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሞያዎች የተቋቋመ አገር በቀል ኩባንያ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።



58060cookie-checkበ10 ዓመት ውስጥ ለ100 ሺሕ የመኖሪያ ቤቶች ለመገንባት የሚያስችል የቤት ኘሮጀክት ይፋ ሆነ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE