በአመት ከ1.2 ቢሊየን በላይ የአሜሪካን ዶላር የሚያመጣ ካምፓኒ ወደ ሥራ ሊገባ እንደሆነ ተገለፀ

Reading Time: 2 minutes
ቀንጢቻ ማይኒንግ ፒኤልሲ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የሊቲየም ማእድን በማውጣት ለሃገራችን ኢትዮጵያ በአመት ከ1.2 ቢሊዮን በላይ የውጭ ምንዛሪ ለማምጣት እንደሚሠራ የገለጸው ዛሬ ነሐሴ 9 ቀን 2015 በሸራተን አዲስ በተደረገው ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ለሼር ሆልደሮቹ በተደረገው የትውውቅና እውቅና መርሐግብር ላይ ነው።

በዚህ መርሐግብር ላይ የቀንጢቻ ማይኒንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር መስራች እና ከፍተኛ ባለ አክስዮን የሆኑት ሃጂ አሊ ሁሴን እንደተናገሩት በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የኸነውን እና በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የተገዛውን ፕሮሰሲንግ ፕላንት በመጪው መስከረም ወር በማስገባት ሥራ ለመጀመር እንደታቀደ ገልፀዋል ።

በተጨማሪም ሁለት ከፍተኛ አቅም ያላቸው ፕሮሰሲንግ ፕላንቶች በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ከመገባደዱ በፊት (ከታህሳስ ወር) አስቀድሞ በማስገባት በጠቅላላው በሰዓት 270 ሺ ቶን ሊትየም በማምረት ከከፍተኛ አምራቾቹ ራሻና ቻይና ተርታ ለመሰለፍ እየሰራ እንደሚገኝ ሀጂ አሊ ሁሴን ጠቅሰዋል።

ሊትየም ማዕድን በዋንኛነት ለመኪና፣ ለሞባይል እና ለላፕቶፕ ባትሪ መሥሪያነት የሚያገለግል ማዕድን ሲሆን የቀንጢቻ ማይኒንግ ፒኤልሲ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው የሊቲየም ማእድን ማለትም የተፈጥሮ ነዳጅ ምትክ ማእድን ለማውጣት ዝግጅቱን ጨርሶ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑን ገልጸዋል።

ዓለም የነዳጅ መኪና ትቶ ወደ ኤሌክትሪክ መኪና እየዞረ ነው፡፡ የሶላር ኢነርጂ እጅግ ተፈላጊ የሃይል ምንጭ እየሆነ መጥቷል።

የኤሌክትሪክ መኪኖችም ሆኑ የሶላር ሃይል ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ዋነኛ ግብዓታቸው ይህ የሊቲየም ማእድኑን ሲሆን ለማውጣት 80 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር ኢንቨስትመንት አድርጎ ወደ ስራ ገብቷል።

ቀንጢቻ ማይንኒግ ሊቲየም የባትሪ ምርት ዋነኛ ግብአት በመሆኑ ማእድኑን ወደ ውጪ እየላከ የበዪ ተመልካች እንዳይሆን የሊቲየም ባትሪ ፋብሪካ ለመክፈትም ጥናቱን አጠናቆ በዝግጅት ላይም ይገኛል፡፡

የሊቲየም ማይኒንግ ስራ ብዙ ሥራ መሥራት የሚጠይቅ ሲሆን ወደታች እስከ አርባ ሺ ሜትር መቆፈርን ይጠይቃል፡፡

ቀንጢቻ ማይኒንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር በሙሉ አቅሙ ስራውን ሲተገብር ይህ የሊቲየም ማእድን ከሀገራችን ከርሰ ምድር ወጥቶ ለዓለም ገበያ ሲቀርብ ኢትዮጵያ በዓመት 1.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ የምታገኝ ሲሆን ለ500 ኢትዮጵያውያን የስራ እድል ይከፈትላቸዋል።

ይህ ኩባንያ የሚገኘው በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን በሰባ ቦሩ ወረዳ እንደሚገኝ በመርሐግብሩ ተገልጿል ።

በዚህ መርሐግብሩ ላይ ለኩባንያው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ መንግሥታዊ አካላትና ግለሰቦች ሽልማት የተቀበሉ ሲሆን ቀንጢቻ ማይኒንግ ለሰባ ቦሩ ዞን የ2 ሚለየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

57910cookie-checkበአመት ከ1.2 ቢሊየን በላይ የአሜሪካን ዶላር የሚያመጣ ካምፓኒ ወደ ሥራ ሊገባ እንደሆነ ተገለፀ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE