በ1952 ዓ.ም የተመሠረተችው የሰምጥ ሸለቆዋ ሐዋሳ ከተማ በቀደመው የሲዳሞ ክፍለ ሀገር ገዥ በነበሩት በልዑል ራስ መንገሻ ስዩም አማካኝነት እንደተቆረቆረች በስፋት ይነገራል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ስማቸው ጎልቶ ከሚነሱ ከተሞች መካከል በቀዳሚነት ተርታ የምትገኘው ሐዋሳ ከባሕር ጠለል በላይ በአማካኝ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሜትር ከፍታ ስትገኝ ከአዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ ወደ ኬንያ በሞያሌ በኩል በሚወስደው መስመር 275 ኪሎ ሜትሮችን ርቃ ትገኛለች።
ሐዋሳ ስያሜዋን ያገኘችው ለውበቷ ካባ ሁኖ ዙርያዋን ከከበባት ሀዋሳ ሐይቅ ነው፡፡ሐይቁ በስተሰሜን ምዕራብ በኩል ከተማዋን የሚያዋስናት ሲሆን ይህ ሐይቅ ከ157 ነጥብ ስኩዮር ኪሎ ሜትር ስፋት ላላት ሐዋሳ የዜጎቿ መተዳደርያ፣ የጎብኝዎቿ ቀልብ መግዣ፣ የውበቷ ዘውድ ነው፡፡ የሐዋሳ ሐይቅ 16 በ 9 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ጠሀት ላይ የአሳ ገቢያ ፤ ምሽት ላይ ደግሞ የጸሀይ መጥለቅ የጎብኝዎችን ቀልብ ይስባል።
ሐዋሳ ከተማ የሲዳማ የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ ፣ የመስቀል፣ የጥምቀት ፣ ታህሳስ እና ሐምሌ 19 ቀን የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በዓል አስመልክቶ በጣም በርካታ የሀገር እና የውጪ ሀገር ጎቢኚውች ይተማሉ።
የቅድስ ገብርኤል ህንጻ ቤተክርስቲያን ፣የሲዳማ ሱሙዳ ሐውልት ፣ የታቦር ተራራ የሐዋሳ ሐይቅ ለከተማዋ መለያ ምልክቶች ናቸው ።
ከተማዋ 1952-1960 የአቤላ ወረዳ ርዕሰ ከተማና በ1960 ዓ.ም አካባቢ የሲደሞ ክፍለ ሀገር ዋና ከተማ በመሆን ያገለገለች ሲሆን በ 1954 ዓ.ም በማዘጋጃ ቤትነት ተመዝግባለች፡፡
“ሐዋሳ” የሚለዉ የከተማዋ ስያሜ ከሐዋሳ ሐይቅ ስም የተወሰደ ሲሆን ሐዋሳ ማለት በሲደምኛ ቋንቋ ሰፊ የዉሃ አካል ማለት ነዉ፡፡
ከተማዋ ከመመስረቷ በፊት ስፍራዉ ”አዳሬ” በመባል የሚታወቅ ሲሆን ትርጉሙም በሲዳምኛ ቋንቋ የከብቶች መዋያ ማለት ነዉ፡፡
ሰሞኑን የትራንስፎርሜሽን ሙዚቃና ማስታወቂያ ድርጅት
ባዘጋጀው ሁነት ላይ ተገኝተን የሐዋሳ ከተማ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ተመልክተናል።
በሐዋሳ ከተማ ጥሩ ጊዜ እንድናሳላፍ ላደረጋችሁ አካላት ተቋማት እና ግለሰቦች በሙሉ ከልብ እናመሠግናለን። በተለይ ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ ፣ጋዜጠኛ ፍሬው አበበ፣ የሁነቱ አዘጋጅ አርቲስት ሚኪ ነጋሶ ምስጋናዬ ወደር የለውም። ለቆይታችን ድምቀቶች የነበራችሁ የኪነጥበብ እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጣችሁ።
በፎቶ ግራፉ በኩል ከሞገስ በስተቀር (ፎቶ ስለማይሰጥ) ዋልቴ ፣ ሲስ፣ ተስፍሽ እና ኤፋ ተረባርበዋል።
575400cookie-checkየስምጥ ሸለቆዋ ፈርጥ – ሐዋሳno