« ነገን ዛሬ እንትከል » የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኪነ-ጥበብ እና የመገናኛ ብዙሃባለሙያዎች፣ አትሌቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ ታቦር ተራራ ላይ ተካሄደ።
የትራንስፎርሜሽን ሙዚቃና ማስታወቂያ ድርጅት ከተባባሪ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት ያዘጋጁት የችግኝ ተከላ ለአራተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መርሀ ግብሮችን በአርባምንጭ ፣ በቢሾፍቱ እና በዱከም ከተሞች እንዲሁም ዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የመገናኛ ብዙሃን ፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ አትሌቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት ተከናውኗል።
ሐዋሳን ፍጹም ሰላማዊ፣ ለኑሮ ተስማሚ፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ከተማ ለማድረግ እየሰራን እንገኛለን ያሉት በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከተማዋን ስማርት ከሚያደርጉ ኘሮጀክቶች መካከል የታቦር ተራራ፣ የሐዋሳ መግቢያ በር እና ሌሎችም እንደሚጠቀሱ ገልጸው ከተማዋን ለአለም የሰላም ተምሳሌት በሚያደርግ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የኘሮግራሙ አጋር አካል በመወከል የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ስራ አስፈጻሚ ተወካይ የሆኑት አቶ ፍጹም ከተማ በ8 ዓመታት ውስጥ ከ13 በላይ ፓርኮችን በተለያዩ ቦታዎች መገንባት እንደተቻለ የገለጹ ሲሆን በዚህ አረንጓዴ አሻራ መርሀግብሩ በተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ ፓርኮችና ከተማዎች ጋር በመተባበር ከ15 ሚሊዬን በላይ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ገልጸዋል።
“ኑ ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መነሻ ሀሳብ የተሰናዳው የችግኝ ተከላ መርሐግብሩ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማት ፣ ግለሰቦች ፣ የኪነጥበብ እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እውቅና ተሰጥቷል።
የችግኝ ተከላው መርሐግብር የትራንስፎርሜሽን ሚዲያና አድቨርታይዝንግ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር እና ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በመቀናጀት መዘጋጀቱን
ገልጸዋል።
(ጌች ሐበሻ)
575200cookie-check“ነገን ዛሬ እንትከል” – በሐዋሳ ከተማno
የትራንስፎርሜሽን ሙዚቃና ማስታወቂያ ድርጅት ከተባባሪ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት ያዘጋጁት የችግኝ ተከላ ለአራተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መርሀ ግብሮችን በአርባምንጭ ፣ በቢሾፍቱ እና በዱከም ከተሞች እንዲሁም ዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የመገናኛ ብዙሃን ፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ አትሌቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት ተከናውኗል።
ሐዋሳን ፍጹም ሰላማዊ፣ ለኑሮ ተስማሚ፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ከተማ ለማድረግ እየሰራን እንገኛለን ያሉት በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከተማዋን ስማርት ከሚያደርጉ ኘሮጀክቶች መካከል የታቦር ተራራ፣ የሐዋሳ መግቢያ በር እና ሌሎችም እንደሚጠቀሱ ገልጸው ከተማዋን ለአለም የሰላም ተምሳሌት በሚያደርግ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ
“ኑ ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መነሻ ሀሳብ የተሰናዳው የችግኝ ተከላ መርሐግብሩ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማት ፣ ግለሰቦች ፣ የኪነጥበብ እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እውቅና ተሰጥቷል።
የችግኝ ተከላው መርሐግብር የትራንስፎርሜሽን ሚዲያና አድቨርታይዝንግ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር እና ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በመቀናጀት መዘጋጀቱን
ገልጸዋል።
(ጌች ሐበሻ)
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን