ማዶ ሆቴል እና ፍሬንድ ሺኘ ሆቴል ዛሬ ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በማዶ ሆቴል በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት በበይነ መረብ ላይ ከሆቴሎቹ እውቅና ውጪ “ጌይ ፍሬንድሊ ሆቴል ” በሚል የሆቴሎቻቸው ስም ዝርዝር መካተቱ እና ይህንን መሠረት በማድረግ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መጠቀሱ አግባብ አለመሆኑን ገለገልጸዋል።
የማዶ ሆቴል የሰው ኃይል አስተዳደር ኃላፊ አቶ ሀዲስ ታደሰ እንደገለጹት ሆቴሉ የኢትዮጵያ ባህል ፣ እምነት እና ህግ በተከተለ መልኩ ለደንበኞቻችን አገልግሎት በመስጠት የሚገኝ ሲሆን ፤ ትርፍ ከማገኘት ባሻገር የህብረተሰብን ጤና የተገልጋዩችን ደህንነት የሚጎዳ ነገር ማድረግ አንፈልግም ያሉት ኃላፊው በቅርብ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ድረገጾች ከተመሣሣይ ጾታ ጋር በተያያዘ ስማቸው ከተጠቀሱ በከተማችን ካሉ ከአንድ መቶ በላይ ሆቴሎች ዝርዝር ውስጥ መጠቀሱ የተቋሙን ሰራተኞች እና ደንበኞቻችንን አሳዝኗል ብለዋል።
የማዶ ሆቴል ፍሮንት ኦፊስ ማናጀር ወ/ሮ ረድኤት ወልደገብርኤል እንደገለጹት ተቋሙ የሆቴልን ህግ እና ደንብ ጠብቆ የሚሠራ ሲሆን በተመሳሳይ ጾታ ላይ ግልጽ የሆነ አቋም እንዳለው እና ከዚህም አልፎ ጥንዶችን በአግባቡ እና ህጋዊ በሆነ መንገድ ለማስተናገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዳላቸው ገልጸው ደንበኞቻችን ስጋት እንዲገባቸው ሆነ መጥፎ እይታ እንዲኖራቸው አንፈልግም ብለዋል።
የፍሬንድሺኘ ሆቴል የእንግዳ አቀባበል ኃላፊ አቶ ምንውየለት ታደሰ በበኩላቸው ባለፉት ቀናቶች በማህበራዊ ትስስር ድረገጾች ላይ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር በተያያዘ የሆቴሉን ስም ማጉደፉን ገልጸው ይህ የኢትዮጵያ ባህል ያልሆነውን የተመሳሳይ ጾታ ተግባር እኛም የምንቃወመው ከመሆኑ ባሻገር ይህ ተግባር በሆቴላችን እንዳይፈጸም ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የማዶ እና የፍሬንድሺኘ ሆቴል በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚነሱ አጀንዳዎች ህብረተሰብ ከመነሻው ማጥራት እንዳለበት አሳሰበው ተቋማቶቹ ተመሣሣይ ጾታ እንደማይደግፉ በግልጽም እንደሚያወግዙ ገልጸዋል።
573200cookie-checkግብረሰዶማዊያንን በግልጽ እንደሚቃወሙ የማዶ እና የፍሬንድ ሺኘ ሆቴሎች ገለጹ።no