የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አቋርጦት የነበረው እርዳታ በተወሰነ መልኩ ማቅረብ መጀመሩ ተገለጸ

Reading Time: < 1 minute




በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ወደ ኢትዮጵያ ሲያቀርበው የነበረው የሰብአዊ እርዳታ ከአምስት ወራት በኋላ በአነስተኛ መጠን በድጋሚ መላክ መጀመሩን አሶሸትድ ፕረስ ዘግቧል።

በዚህም መሰረት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች አነስተኛ የእርዳታ ስርጭት መጀመሩ የተገለጸ ሲሆን፤ መንግሥት በሂደቱ ላይ ሚናውን ስለመወጣቱ ድርጅቱ ዕውቅና ሰጥቷል፡፡

ተቋሙ እርዳታውን በማቋረጡ የተለያዩ የግብረሰናይ ድርጅቶች እና የጤና ባለሙያዎችን “በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የእርዳታ እገዳው “ኢ-ሞራላዊ ነው” ሲሉ መተቸታቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡

በአንጻሩ ልክ እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም ኹሉ የሰብአዊ እርዳታዋን ያቋረጠችው ዩናይትድ ስቴትስ እገዳው እንደሚቀጥል የገለጸች ሲሆን፤ ለረዥም ጊዜ በክልል ባለስልጣናት ቁጥጥር ሥር የሚገኘውን አሰራር ለማሻሻል የሚደረገው ድርድርን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እንደምታካሄድ አስታውቃለች፡፡

የአሜሪካ እርዳታ ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፓወር “ተፈጠሩ የተባሉ ችግሮችን በማጣራት እንዲሁም እርዳታው ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በትክክል መድረሱን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ የሰብአዊ እርዳታው በአጭር ግዜ ለማስጀመር ጥረት ይደረጋል ሲሉም አክለዋል፡፡

ተቋማቱ እርዳታውን በማቋረጣቸው ምክንያት ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀጥር አንድ ስድስተኛው ወይም 20 ሚሊዮኑ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ የገለጸው ዘገባው፤ ከዚህ በተጨማሪ ስምንት መቶ ሺሕ ያህሉ ስደተኞች መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል በአራት ቅርንጫፎች፣ ለ100 ሺሕ ያህል እርዳታ ፈላጊ ዜጎች ከፈረንጆች ሐምሌ 31/2023 ጀምሮ አዲሱ የተቋሙ አሰራር ትግበራ ሙከራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት የዓለም ምግብ ፕሮግራም አዳዲስ እርምጃዎች፤ ተጠቃሚዎችን በዲጂታል መመዝገብ፣ በእህል ከረጢቶች ላይ ምልክቶችን መጨመር፣ የግብረመልስ የስልክ መስመሮች እና ለእርዳታ አጋሮች ተጨማሪ ስልጠናዎችን ያካትታሉ ተብሏል።

ኤጀንሲው አዲሱን የማከፋፈያ ስርዓቱን በተቻለ ፍጥነት ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ለማስተላለፍ ተስፋ እንዳለው የገለጸ ሲሆን፤ እርምጃዎቹ የምግብ አቅርቦትን በጣም ለሚያስፈልጋቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዙ እምነት አለኝ ብሏል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ ሲያቀርበው የነበረው የሰብአዊ ድጋፍ ስርቆት እና ላልተገባ ተግባር ውሏል መባሉን ተከትሎ ከአምስት ወራት በፊት የሚሰጠው እርዳታ ማቋረጡ ይታወሳል፡፡

57100cookie-checkየዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አቋርጦት የነበረው እርዳታ በተወሰነ መልኩ ማቅረብ መጀመሩ ተገለጸ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE