ኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ በ1996 ዓ.ም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በቀድሞ የጋሞ ጎፋ ዞን ቦንኬ ወረዳ ኮሸሌ በተባለች ቀበሌ ከ1500 ሄክታር ያላነሰ የእርሻ መሬት በመውሰድ በእርሻ ልማት ስራ ለመስራት ፍቃድ ወሰዶ ስራ የጀመረ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን በወቅቱ ከአለው ሰፊ ሄክታር መሬት ውስጥ ውስን ሄክታር የእርሻ መሬት የሙዝ ተክል በመትከል ስራ የጀመረ ሲሆን ለስራው ማጠናከሪያ እንዲሆን ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ መጋቢት 20 ቀን 2002 ዓ.ም በተፈረመ ዋና የብድርና የመያዥ ውል እንዲሁም መስከረም 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተፈረመ የማስፋፊያ ብድርና የክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ ውል ስምምነቶች መሠረቶ የገንዘብ ብድር ብር 48,007,082.53(አርባ ስምንት ሚሊዮን ሰባት ሺህ ሰማኒያ ብር ከሃምሳ ሶስት ሳንቲም) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ማኀበር ሰጥቷል። ሆኖም ግን በወቅቱ የብድር ገንዘብ ይሰጥ እንጂ ድርጅቱ ውል እስከተቋረጠበት 2012 ዓ.ም ማለትም ከ15 ዓመት በላይ በተሰጠው የኢንቨስትመንት መሬት ላይ ይኸ ነው የሚባል አመርቂ የሚባል ስራ አልተሰራም ሲሉ የጋሞ ዞን ኢንቨስትመንት ቢሮ እና የገረሴ ዙሪያ ወረዳ አመራሮች ይገልጻሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቀን 15/11/2015 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር ኦል/2015/19 ኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባንቢስ አከባቢ በሚገኘዉ የዲኦሎፖል ሆቴል ጋዜጠኞች እንዲገኙ ጥሪ በማስተላለፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቶ ነበር።
የድርጅቱ ባለቤት አቶ ልዑል ስብሃቱ እና የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ቀለሟ አለሙ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት ከሆነ ” በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ ኮሸሌ ቀበሌ የሚገኘው የእርሻ ልማት እና ሀብቱ በአስተዳደር በደል ችግር ምክንያት በርካታ ሀብቶቹንና በህግ አግባብ የተረከበውን መሬቱን እየተቀሙ እንደሚገኝ ” የገለጹ ሲሆን ” ለደረሰብን የፍትህ መጓደል ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ፣ ለብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለደህንነት ቢሮ ዶክመንት ብናስገባም የመንግስት ምላሽ ዘግይቶብናል ” ብለዋል እንዲሁም ” 46 ሚሊዮን ብር የተበደርንበት መሬት እየተቆረጠ እና እየተሸነሸነ እየተዘረፈና እየተሸጠ ይገኛል እስካሁን ከ500 ሚሊየን ብር በላይ በአደባባይ ተዘርፈናል” ብለዋል።
በተጨማሪም ” የባንክ ወለዱ እዳ ምንም ሳንሰራ በቀን 40 ሺህ ብር እየወለደ በአጠቃላይ 102 ሚሊዮን ብር እንደደረሰ በወቅቱ አቶ ልዕል የገለጹ ሲሆን ከ1500 ሄክታር ውስጥ 238 ሄክታር ሙዝ በአካባቢው ባሉ አመራሮች ወድመዋል። ከዚህም በተጨማሪም ሁለተኛው እርሻ ምዕራብ አባያ ቆርጋ የሚባል ቦታ ላይ 200 ሄክታር መሬት የለማ መሬት 37ሄክተር ሙዝ የደረሰ ሽያጭ የጀመረ ኢፍትሀዊ በሆነ የአስተዳደር በደል ለሌላ ባለ ሀብት ከነ ንብረቶቹ ተሰጥቷል ” ያሉ ሲሆን ” ሶስተኛው እርሻችን እዛው ጋሞ ጎፋ ዞን ደረማሎ ወረዳ ከልማት ባንክ በጨረታ አሸንፈን የገዛነው 485 ሄክታር መሬት ገዝተን ያለማነውን ቦታ ኢፍትሀዊ በሆነ የአስተዳደራዊ ሸር እና ተንኮል ጥለን እንድንወጣም ተደርጓል ” ሲሉ በወቅቱ ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት መግለጫ ሰጥተው ነበር ።
በወቅቱ ባለሃብቱ የሰጡትን መግለጫ መነሻ በማድረግ የዝግጅት ክፍላችን በጋሞ ዞን የሚገኙ የዞን እና የወረዳ የስራ ኃላፊዎችን ከስራው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ባለሙያዎችን በአካል ቦታቸው ድረስ በመሄድ አናግረናል።
በቀድሞ የጋሞ ጎፋ ዞን ቦንኬ ወረዳ በአሁኑ አጠራር በጋሞ ዞን የገረሴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝጌ ካሣ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ላይ እንደገለጹት “በቀድሞ ማኑዋል 2000 ሄክታር በአዲሱ የዲጅታል ሲለካ 1500 ሄክታር መሬት ለኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተሰጠ ሲሆን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከ14 አመት በላይ ከ30 ሄክታር ያልበለጠ ቦታ ላይ ሙዝ ከማምረት ባሻገር ምንም አይነት የእርሻ ልማት እየሰሩ ባለመሆናቸው እና ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ብንሰጥም ምንም አይነት ማሻሻያ ባለመደረጉ ከዚህም አልፎ ተርፎም ለወረዳው ገቢ መደረግ የነበረበትን የሰራተኞች የስራ ግብር በወቅቱ ባለመክፈሉ እንዲሁም በእርሻ ቦታው ላይ የነበሩ ማሽነሪዎችን እና የተሽከርካሪ አካላትን ጭምር በማሸሻቸው ከ2012 ጀምሮ ወረዳው ከኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ የነበረውን ውል እንዳቋረጠ” ገልጸዋል።
” ኦልግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ወደ አካባቢው ገብቶ በርካታ የልማት ስራዎችን ይሰራሉ ብለን ብንጠብቅም ወረዳውም ሆነ የአካባቢው ማኀበረሰብ ለ14 አመታት ከኢንቨስትመንቱ ተጠቃሚ ሳይሆኑ “እንደቀረ አቶ አዝጌ ካሣ ለዝግጅት ክፍላችን የገለጹ ሲሆን ” በወቅቱ የነበሩ የወረዳው ባለሙያዎች እና አመራሮች ለኦልግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ ቢሹም የኢንዱስትሪው አመራሮች እና ባለቤቶች በአካል ሊገኙ እንዳልቻሉ” የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝጌ ካሣ የገለጹት።
በቀድሞ የቦንኬ ወረዳ የገቢዎች ኃላፊ እንዲሁም የወረዳው አስተዳደር በአሁኑ መዋቅር የገረሴ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ካሳሁን ዋሲሁን ” ኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ በወቅቱ የእርሻ እና የመሬት መጠቀሚያ ግብር ባለመክፈሉ ከፍተኛ ውዝግብ የነበረ ሲሆን እርምጃ ለመውሰድ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደገቡ” ገልጸዋል።
የኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ባለሀብት አቶ ልዑል ስብሃቱ በወረዳው አመራሮች ከሌሎች ባለሀብቶች ጋር በመመሳጠር በእርሻው ላይ ገንዘብ ያወጣሁባቸው ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ በአደባባይ ተዘርፏለሁ ብለው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል ለመሆኑ ይህ ለምን ተፈጸመ ብለን ለአቶ ካሳሁን ዋሲሁን ከዝግጅት ክፍላችን ለቀረበላቸው ጥያቄ እንዳብራሩት “ምንም አይነት የአስተዳደር በደል አልተፈጸመም በወቅቱ ሌላ ባለሃብት ያልነበረ ሲሆን ከሌላ ባለሃብት ጋር በመቀናጀት በእሳቸው ላይ ጫና የምናደርስበት ሁኔታ ሊኖር እንደማይችል” ገልጸዋል። “ባለሃብቱ ከ1996 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምንም ሳያመርቱ፣ ለህብረተሰቡና ለአርሶ አደሩ ምንም መሰረተ ልማት ሳይገነብ ነው የቆየት ተፅዕኖ ቢደረግባቸውም ኖሮ ይሄን ያህል ጊዜ አይቆዩም” ሲሉ ገልጸዋል።
ማንነትን መሠረት በማድረግ ጥቃት ደርሶብኛል ለሚለው የባለሀብቱ ጥያቄ አቶ ካሳሁን ዋሲሁን በምላሹ “እኔ በነበርኩበት ወቅት የድርጅቱ እዳ ክፈሉ ተብለው ከመጠየቃቸው ባለፈ ብሄር ተኮር ጥቃት አልተደረገባቸውም ይህም የአካባቢው መገለጫ አለመሆኑን ” ገልጸዋል።
አቶ ታምራት ጎአ በቀድሞ የቦንኬ ወረዳ የንግድ ኃላፊ በአሁኑ ደግሞ የገረዜ ወረዳ ገቢዎች ኃላፊ ናቸው እርሳቸው እንደሚሉት “ወረዳው ከኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ማግኘት የነበረበትን ከ2013 በፊት ያልተከፈለ የሰራተኛ ግብር ከ593 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አጥቷል። በዚህም የተነሳ ወረዳው አሁን ላይ ለመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አልቻለም፤ በጣም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያሉት ኃላፊው ገንዘብን ለማስመለስ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ቢገኙም መሬቱን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ሌሎች ግለሰቦች የይገባኛል ጥያቄ እንዳቀረቡበት” ገልጸዋል።
በሌላ በኩል አቶ ወልዴ ጎንቦ ከኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ
በቦንኬ ወረዳ ኮሸሌ ቀበሌ ላለው የእርሻ መሬት ላይ የሚሰሩ ግንባታቸው የተጠናቀቀ የውሃ ተፋሰስ ፣ 30 በ 15 ሜትር በድንጋይ የተሰራ ከፍታው አምስት ሜትር የሆነ ትልቅ መጋዝን ፣ 25 በ8 ሜትር በድንጋይ የተገነባ የሠራተኛ መኖሪያ ፣ 24 በ12 ሜትር ግንባታው ያልተጠናቀቀ የሠራተኞች መመገቢያ ለመስራት ውል በመዋዋል በወቅቱ ስራ ጀመረው የነበረ ቢሆንም በወቅቱ የሚገባኝን እና የሰራሁበትን ከ700 ሺህ ብር በላይ የተከፈለኝ ሲሆን ቀሪ 430 ሺህ ብር ኦል ግሪን አልከፈለኝም ሲሉ ቅሬታቸውን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። ግለሰብ ያነሱት ጥያቄ መሠረት በማድረግ የኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ባለቤት አቶ ልዑል ስብሃቱ ከድሬ ቲዮብ እና ከአዲስ ቪው ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት “የቀረ ምንም አይነት ክፍያ አለመኖሩን ” ገልጸዋል።
አቶ ልዑል ስብሐቱ ከድሬ ቲዮብ እና ከአዲስ ቪው ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ” የደረሰብንን በደል የፌደራል መንግስት በተለይ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አጣሪ ኮሚቴ አዋቅሮ እኛም ባለንበት ቦታው ድረስ በመሄድ ወረዳው ላይ የወደሙ እና ከባንክ በግል ጨረታ የገዛናቸው ንብረቶቻችንን ካሳ እንዲከፈለን ፣ መመሪያው ተፈጻሚ እንዲሆን በተጨማሪ እኛም አጥፍተን ከሆነ በሌላ በኩል ያጠፋ አካል ተጣርቶ ተገቢው ሕጋዊ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ” ጠይቀዋል።
የገረሴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝጌ ካሣ ወረዳው ከባህር ጠለል በላይ ከ600- 3200 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቆላ ወይና አደጋ እና ደጋ የአየር ንብረት ይዛል። የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ጤፍ ፣ ሙዝ ፣ ሰሊጥ ፣ማሽላ፣ ባቄላ ፣ አተር ፣ስንዴ ፣ ገብስ እና የመሳሰሉት ምርቶች የሚበቅሉበት መሆኑን የገለጹ ሲሆን ባለሀብቶች በማዕድን፣ በግብርናው ፣ በንግዱ ፣ በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፎች በመምጣት እንዲያለሙ አሳስበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሐምሌ 29 ቀን 2015 በማኀበራዊ ትስስር ድረገጹ ላይ እንዳስነበበው ከሆነ የጋሞ ዞን ኢንቨስትመንት አስፈፃሚ ኮሚቴም ባደረገው ውይይት ኦልግሪን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፈቃድ እንዲሰረዝ በመግባባት 1000 ሄክታር መሬት ለኦሞቲክ ጠቅላላ ንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲሰጥ ቀሪው 500 ሄክታር ደግሞ የቀደመው ፕሮጀከት ከልማት ባንክ ለተበደረው ገንዘብ ማስያዣነት እንዲሰጥ መወሰኑን የተገለጸ ሲሆን የኦሞቲክ ቢዝነስ ግሩፕ በወረዳው ለሚተገብረው ፕሮጀክት በ75 ሚሊዮን ብር ካፒታል በማስመዝገብ ሥራውን የጀመረ ሲሆን ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የእርሻ ማሽነሪዎች በመግዛት በተረከበ በአጭር ጊዜ ከ300 ሄክታር በላይ መሬት አልምቷል ሲል የዞኑ መንግስት ኮምንኬሽን ገልጿል።
567800cookie-checkከ500 ሚሊዮን ብር በላይ በአደባባይ ተዘርፏለሁ ! / ኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ/ ምንም አይነት የአስተዳደር በደል አልተፈጸመም ! /የገረሴ ወረዳ አስተዳደር /no
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቀን 15/11/2015 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር ኦል/2015/19 ኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባንቢስ አከባቢ በሚገኘዉ የዲኦሎፖል ሆቴል ጋዜጠኞች እንዲገኙ ጥሪ በማስተላለፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቶ ነበር።
የድርጅቱ ባለቤት አቶ ልዑል ስብሃቱ እና የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ቀለሟ አለሙ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት ከሆነ ” በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ ኮሸሌ ቀበሌ የሚገኘው የእርሻ ልማት እና ሀብቱ በአስተዳደር በደል ችግር ምክንያት በርካታ ሀብቶቹንና በህግ አግባብ የተረከበውን መሬቱን እየተቀሙ እንደሚገኝ ” የገለጹ ሲሆን ” ለደረሰብን የፍትህ መጓደል ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ፣ ለብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለደህንነት ቢሮ ዶክመንት ብናስገባም የመንግስት ምላሽ ዘግይቶብናል ” ብለዋል እንዲሁም ” 46 ሚሊዮን ብር የተበደርንበት መሬት እየተቆረጠ እና እየተሸነሸነ እየተዘረፈና እየተሸጠ ይገኛል እስካሁን ከ500 ሚሊየን ብር በላይ በአደባባይ ተዘርፈናል” ብለዋል።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
በወቅቱ ባለሃብቱ የሰጡትን መግለጫ መነሻ በማድረግ የዝግጅት ክፍላችን በጋሞ ዞን የሚገኙ የዞን እና የወረዳ የስራ ኃላፊዎችን ከስራው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ባለሙያዎችን በአካል ቦታቸው ድረስ በመሄድ አናግረናል።
በቀድሞ የጋሞ ጎፋ ዞን ቦንኬ ወረዳ በአሁኑ አጠራር በጋሞ ዞን የገረሴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝጌ ካሣ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ላይ እንደገለጹት “በቀድሞ ማኑዋል 2000 ሄክታር በአዲሱ የዲጅታል ሲለካ 1500 ሄክታር መሬት ለኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተሰጠ ሲሆን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከ14 አመት በላይ ከ30 ሄክታር ያልበለጠ ቦታ ላይ ሙዝ ከማምረት ባሻገር ምንም አይነት የእርሻ ልማት እየሰሩ ባለመሆናቸው እና ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ብንሰጥም ምንም አይነት ማሻሻያ ባለመደረጉ ከዚህም አልፎ ተርፎም ለወረዳው ገቢ መደረግ የነበረበትን የሰራተኞች የስራ ግብር በወቅቱ ባለመክፈሉ እንዲሁም በእርሻ ቦታው ላይ የነበሩ ማሽነሪዎችን እና የተሽከርካሪ አካላትን ጭምር በማሸሻቸው ከ2012 ጀምሮ ወረዳው ከኦል ግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ የነበረውን ውል እንዳቋረጠ” ገልጸዋል።
” ኦልግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ወደ አካባቢው ገብቶ በርካታ የልማት ስራዎችን ይሰራሉ ብለን ብንጠብቅም ወረዳውም ሆነ የአካባቢው ማኀበረሰብ ለ14 አመታት ከኢንቨስትመንቱ ተጠቃሚ ሳይሆኑ “እንደቀረ አቶ አዝጌ ካሣ ለዝግጅት ክፍላችን የገለጹ ሲሆን ” በወቅቱ የነበሩ የወረዳው ባለሙያዎች እና አመራሮች ለኦልግሪን አግሮ ኢንዱስትሪ ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ ቢሹም የኢንዱስትሪው አመራሮች እና ባለቤቶች በአካል ሊገኙ እንዳልቻሉ” የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝጌ ካሣ የገለጹት።
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ