ኦክሎክ ሞተር በ1.5 ቢሊዮን ብር በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቼራሊያ አካባቢ ያስገነባውን ዘመናዊ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ዛሬ ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም አስመርቋል።
ኦክሎክ ጀኔራል ትሬዲንግ በኢትዮጵያ የመኪና ኢንዱስትሪ ዘርፍ እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ይዞ የተደራጀ ሲሆን ገና ከጅምሩ 200 አይነት ሞዴል መኪናዎችን መገጣጠም የቻለ ተቋም ሲሆን የድርጅቱ መስራች አህመዲን መሀመድ ገና በልጅነቱ ከወፍጮ ቤት እቃዎች ስራ እስከ መገጣጠም በደረሰ ዝቀተኛ ደረጃ ላይ የነበረ ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ አዳዲስ ማሽኖችን ማምረት መገጣጠም ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሲሆን በመቀጠልም ወደ መኪና ቴክኖሎጂ በመሸጋገር በመኪና ላይ የጥገናና የመገጣጠም ስራን በማከናወን ረጅም አመታት ተጉዘዋል።
ኦክሎክ በ14 ሚሊዬን መነሻ ካፒታል የተመሠረተ ሲሆን
ድርጅቱ ከ250 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ዜጎችን በቋሚነት እና በጊዚያዊነት የስራ እድል ተፈጥሯል።
ኦክሎክ ሞተርስ ሲመረቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
ኦክሎክ ሞተርስ ለሀገራችን ኢትዮጵያ በዘርፉ ዘመናዊነትን ለማላቀስና ውጤታማ የመኪና ቴክኖሎጂ እድገት ለማምጣት በማለም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራርሟል።
567600cookie-checkኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተመረቀ።no