“ሠላም “የአዲስ አመት ሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው።

Reading Time: < 1 minute
ሸራተን አዲስ ሆቴል እና ይሳቃል ኢንተርቴይመንት በጥምረት ያዘጋጁት የአዲስ አመት የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ጳጉሜ 6 ቀን 2015 ዓ.ም ማምሻውን በሸራተን አዲስ ሆቴል እንደሚካሄድ ተገለጸ።

አዘጋጆቹ ዛሬ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ሰላም የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ በተለያዩ ዓለማቀፍ መድረኮች አድናቆትን ያተረፈውና በመድረክ ስሙ ሬማ በመባል የሚታወቀው ናይጄሪያዊው ተወዳጅ አፍሮ ቢት ዘፋኝ እና በአዲስ ስልት የኢትዮጵያን ሙዚቃ አፍቃሪ ልብ ያሸነፈው የሂፕ ሆፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ልጅ ሚካኤል እንዲሁም ተዎዳጅዋ እንስት ድምጻዊት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) እና ከፍተኛ አድናቆን እያተረፉ ከመጡ አዳዲስ ድምጻዊያን መካከል አንዱ የሆነው አዲስ ለገሰ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብላል።

የኢትዮጵያን ባህል እና ሙዚቃ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በአለም ላይ በማስተዋወቅ እና እንዲሁም አዳዲስ የመዝናኛ መንገዶችን ለሃገር የሚያስተዋውቀው ይሳቃል ኢንተርቴይመንት የሚዘጋጀው ሠላም የሙዚቃ ኮንሰርት
የመግቢው ዋጋ አሁን ላይ ያልተወሰነ ሲሆን ከ 15ሺህ እስከ 20,000 ሊደርስ እንደሚችል በዛሬው መግለጫ ተነግሯል።
………..

56720cookie-check“ሠላም “የአዲስ አመት ሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE