ከተመሰረተ 5ኛ አመቱን የያዘው ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ በአዲስ አበባ ቦሌ ለየት ያለ ጂም ቤት መክፈቱን ዛሬ ይፋ አደረገ። የኢትዮ ዳንስ ፊትነስ መስራች እና ባለቤት ቶማስ ኃይሉ (Tommy+) ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ በኢትዮጵያ ባህላዊ ውዝዋዜ ታጅቦ የሚሰራው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጂም ቤቱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 30 ሚሊዮን ብር እንደጨረሰ ተናግሯል።
በኢትዮጵያ ከ83 በላይ የብሄር ብሄረሰቦች ሙዚቃ አለ ከእነዚህ ውስጥ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ የቱ ይሆናል የሚለውን ጥናት አድርጌ የሰራውት ፕላትፎርም ነው ሲል ቶሚ ገልጿል።
አሁን የተከፈተው ጂም ቤት 500 ሰዎችን በአንድ ጊዜ እንዲያስተናግድ ተደርጎ የተገነባ ሲሆን ስቲም፣ ሳውና እና ጂም ያካተተ ነው። የቤቱን መከፈት እና 5ኛ አመቱን ምክንያት በማድረግ እስከ አርብ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓም በነፃ ሁሉም በመምጣት የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን መስራት እንደሚችል ተገልጿል።
ምዝገባ እየተካሄደ ሲሆን ለጊዜው በቀን 500 ሰዎችን ለማስተናገድ ታስቧል፣ እስካሁን 400 ሰው እንደተመዘገበ የተገለፀ ሲሆን የኢትዮ ዳንስ ፊትነስ መገኛ ቦሌ ከዮድ አቢሲኒያ ገባ ብሎ ላክስ አዲስ አከባቢ ይገኛል።
565400cookie-check30 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆነበት ጂም ቤት ተከፈተno