የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ይፋ ሆነ፡፡

Reading Time: 2 minutes
82.16 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዘጠነኛ ክፍል አልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በዛሬው እለት የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ማለፊያ ውጤትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸውም በዘንድሮው ማለፊያ ውጤት 50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዘጠነኛ ክፍል እንደሚዘዋወሩ ጠቁመው የተለያየ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የማለፊያ ነጥቡ 45% መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ 73,385 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደው 70.6% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸውን ዶክተር ዘላለም ገልጸው 61,840 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 50,812 የሚሆኑት ማለትም 82.16 % ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን መዘዋወራቸውን አስረድተዋል፡፡



የዘንድሮው ውጤት ባለፉት አመታት ጋር ሲነጻጸር መሻሻል ማሳየቱን ኃላፊው ጠቁመዋል።

የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2015ዓ.ም ከሰአታት በኋላ ትምህርት ቢሮ ድረገጽ በመግባት የመፈተኛ ቁጥራቸውን ወይም ባር ኮድ በማስገባት መመልከት የሚችሉ ሲሆን በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት ደግሞ የ6ኛ ክፍል ውጤት ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡

56280cookie-checkየ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ይፋ ሆነ፡፡

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE