ደምበል ኮሌጅ ለ4ኛ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ።

Reading Time: 2 minutes
ደምበል ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም በሸገር ከተማ አስተዳደር በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ወጣት ማዕከል አስመረቀ።

ደምበል ኮሌጅ ከተመሠረተበት ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ተማሪዎችን አስመርቆ በስራ ላይ ያዋለ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለ4ኛ ግዜ በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ፣ በሰርቨይንግ ቴክኖሎጂ ፣ በነርሲንግ ፣በፋርማሲ ፣በኢንፎርሞሽን ቴክኖሎጂ እና በአካውንቲንግና ባንኪንግ እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ ግዜ በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ፣ በቢ ኤስ ሲ ነርሲንግ እና በአካውንቲንግና ፋይናንስ በአጠቃላይ 159 ወንድ 198 ሴት በድምሩ 357 ተማርዎችን በቀን እና በማታ መርሐግብር አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡

ደምበል ኮሌጅ ለትምህርትና ስልጠና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የሀገራችን የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በሚያዘጋጀው መስፈርት መሠረት በየጊዜው እያስገመገመ መሻሽያዎችን እያደረገ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ተሸመ በቀለ የደምበል ኮሌጅ ባለቤት እና የቦርድ ሰብሳቢ በምርቃው መርሐግብር ላይ ገልጸዋል።

በዛሬው የምረቃ መርሐግብር ቀን የዕለቱ የክብር እንግዳ የኦሮሚያ ማይኒንግ ጉሩኘ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር መስፍን አሰፋ ለተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

ኮሌጅ ከመደበኛው የመማር ማስተማር ተግባሩ ባሻገር በማህበረሰብ ግልጋሎት እና በጥናት እና ምርምር ስራዎቹ ጠንክሮ እየሠራ እንደሚገኝ የኮሌጅ ዲን አቶ ደመላሽ ከበደ ከምረቃው መርሐግብር በኃላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል፡፡

ደምበል ኮሌጅ ለአካባቢው ማኀበረሰብ በሚሰጠው አገልግሎት ለበርካታ ተማሪዎች ነጻ የትምህርት አድል ከመስጠት ባሻገር በርካታዎችን የሙያ ባለቤቶች በማድረግ የስራ እድል በመፍጠር በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ደምበል ኮሌጅ በሸገር ከተማ አስተዳደር በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማና በሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር ባሉት ሁለት ካምፓሶች በመደበኛ፣ በማታና በርቀት የትምህርት መርሃ-ግብሮች እያስተማረ ሲገኝ በዚህ አመት ጀምሮ በ2ኛ ዲግሪ (ማስተርስ) መርሐግብር በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በማስተርስ ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ እያስተማረ ሲገኝ ከተመሰረተበት ጀምሮ በአጠቃላይ በለገጣፎ ካምፓስ 1609 እና በሰንዳፋ ካምፓስ 1324 በድምሩ 2933 ተማሪዎችን ተቀብሎ አስተምሯል በማስተማር ላይ ይገኛል።

(ጌች ሐበሻ)
ፎቶ፦ ሲሳይ ጉዛይ

56260cookie-checkደምበል ኮሌጅ ለ4ኛ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE