“የኔ መንገድ” መጽሐፍ ተመረቀ።

Reading Time: 2 minutes
“የኔ መንገድ” የተሰኘው በደራሲ ኮሎኔል ፈቃደ ገብረየስ የተፃፈው ግለ ታሪክ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 15 ቀን 2015ዓ.ም በግዮን ሆቴል በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ ተመረቀ።

ከመፅሃፍ አዟሪነት እስከ ኮሎኔል ማዕረግ የደረሱት የ69 አመቱ ኮሎኔል ፈቃደ ገብረየስ በትምህርት ረገድ በሚሊታሪ ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪ እና በቢዝነስ ሥራ አመራር የመጀመሪያ ዲግሪ በማኔጅመንት አሰልጣኝነትና አማካሪነት ሙያዬ ሀገራቸውን ያገለገሉ ሲሆን በርካታ ውጣ ወረዶችን እንዳሳለፉ በመጽሐፍ ምርቃት መርሐግብር ላይ ተገልጿል።

ኮሎኔል ፍቃደ ገብረየስ ከዚህ ቀደም የአመራር ሳይንስና ጥበብ፣ ድርጅታዊ የጤና ምርመራ ፣ የዓለም ሀገሮች፣ ስትራቴጂ ስራ አመራር፣ የተሰኙ መፅሃፍቶችን ለአንባብያን ማቅረባቸው ይታወቃል።

ደራሲ ዘነበ ወላ እና አቶ ባዩልኝ አያሌው አርቲኢ ያደረጉት የኔ መንገድ መጽሐፉ ስምነት ክፍሎች ያሉት ሲሆን 653 ገጾች በ600 የኢትዮጵያ ብር ለአንባቢያን ቀርቧል።

ቴዲአብ ሚዲያ እና ኢንተርቴይመንት አማካኝነት በተሰናዳው በዚህ መጽሐፍ ምርቃት መርሐ ግብር ላይ የተለያዩ ድርጅቶች አመራሮች እና ግለሰቦች ፣ ወታደራዊ አዛዦች፣ ምሁራን፣ የጸሐፊው ቤተሰቦችና ወዳጆች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል።

56240cookie-check“የኔ መንገድ” መጽሐፍ ተመረቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE