ለተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንሰር ኦርጋናይዜሽን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የደም ልገሳ ተከናወነ።

Reading Time: 2 minutes
ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ግሎባል አካባቢ በሚገኘው መዓዛ ደስአለኝ ሕንጻ ለተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንሰር ኦርጋናይዜሽን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የደም ልገሳ አከናውነዋል።

ድርጅቱ በዋነኝነት የህፃናት ካንሰርን ለመከላከል እና ለማከም የሚረዳ ድጋፍ በማድረግ ከአራት የመንግስት ሆስፒታሎች ጋር ይሰራል እነዚህም ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሆስፒታል፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ጋር በመሆን እየሰራ ሲገኝ ማዕከሉ ከተቋቋመ ቀን እንስቶ ከ2000 ታካሚዎች ሕክምናቸውን እንዳይቋረጥ ከማደሪያ አንስቶ እስከ ምግብ፣ መድኃኒት፣ ትራንስፖርት፣ የስነ-ልቦና፣ ትምህርት እና ሆስፒታሎቹ ላይ የሚጎድል ቁሶችን እያገዘ ይገኛል፡፡

የተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንሰር ኦርጋናይዜሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ሣራ ኢብራሂም በመርሃግብሩ ላይ ተገኝተው እንደገለጹት ድርጅቱ ታካሚ ልጆች አንዱ ከነሕክምናው ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጋቸው ደም መሆኑን ያነሱት ስራ አስኪያጇ ታካሚዎች ደም በማጣት ማለት ለሕይወት ማለፍ አንዱ መንስኤ በመሆኑ የካንሰር ታካሚ ልጅ በሕክምናው ሂደት ውስጥ ከ5ዐ ከረጢት በላይ የደም ውጤት እንደሚያስፈልግ ይህንን የሚገኘው ደግሞ በጎ ፈቃደኞ በሚለግሱት ደም በመሆኑ ለዚህም ሁሉም ህብረተሰብ ደም እንዲለግስ አሳስበዋል።

ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንሰር ኦርጋናይዜሽን የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ በፌደራል መስሪያቤቱ ሕግ እና ደንብ መሰረት በአዋጅ ቁጥር 621/2009 መሰረት ተቋቁሞ ኅዳር 26 ቀን 2005 ዓ,ም እና በዳግም ምዝገባ በዐ6/09/2011 በምዝግባ ቁጥር 2920 ተመዝግቦ መንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

56220cookie-checkለተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንሰር ኦርጋናይዜሽን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የደም ልገሳ ተከናወነ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE