የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት መጠናቀቁን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ

Reading Time: < 1 minute

ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት መጠናቀቁን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ኃላፊ ኮሚሽነር ናስር መሐመድ እንደገለጹት በየዓመቱ ሐምሌ 19 ቀን በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በሚገኘው ቁልቢ ገብርኤል የሚከበረው ዓመታዊ የንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከበር ዘንድ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።

ከሃገር መከላከያ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከሐረሪ ክልል፣ ከድሬዳዋ አስተዳደርና ከምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞን የተውጣጣ የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ኮማንድ ፖስት መቋቋሙንና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተገመገሙ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ምዕመኑም የንግስ በዓሉን ለማክበር በሚመጣበት ወቅት በገዳሙ አካባቢ የሠዎች መጨናነቅ ስለሚኖር በመግቢያና መውጫ በሮች፣ ክርስትና ቤት፣ ስለት ማስገቢያ፣ በቤተ መቅደሱ በሮች አካባቢ ወንጀል እንዳይፈፀም ጥንቃቄ እንዲያድርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል የሚከበርበት አካባቢ የመሬቱ አቀማመጥ ዳገታማና ጠመዝማዛማ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ አደጋ እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የትራፊክ ህግና ደንብን አክብረው እንዲያሽከረክሩም ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ከሐምሌ 18 ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ከሰዓት በኋላ ድረስ ከጨለንቆ እስከ ቀርሳ ባሉት ከተሞች ከባድ መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑንና የንግድና የቤት መኪኖችንም በእነዚህ መንገዶች አቁሞ መሔድ የተከለከለ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የወንጀል ድርጊቶች ተፈጽመው ከተገኙ ምዕመናኑ እንዳይጉላላ ሦስት ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያዎችና ዐቃቤ ህግ እና ፍርድ ቤት በማቋቋም አፋጣኝ ፍርድ እንደሚሰጥም
የመምሪያው ኃላፊ ኮሚሽነር ናስር መሐመድ ገልጸዋል።
56050cookie-checkየቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት መጠናቀቁን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE