በጄኔቭ ሲውዘርላንድ ዋና ቢሮውን ያደረገው አይቲ ሶሉሽንስ ሰርቪስ ( ITSS) በኢትዮጵያ ቢሮውን ከፈተ።

Reading Time: < 1 minute
በ 2001 የተመሠረተው እና ዋና መስሪያ ቤቱን በጄኔቭ ስዊዘርላንድ ያደረገው የቴክኖሎጂ ድርጅት ISS በሀገራችን ኢትዮጵያ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎትን በጠንካራ ሁኔታ ለመጨመር ከኢትዮጵያ ድርጅቶች ጋር በአብሮነት እየሰራ እንደሚገኝ እና አዳዲስ አብረው የሚሰሩ ድርጅቶች መኖራቸውን በትላንትናው ዕለት ሀምሌ 13/2015 ዓ/ም በካፒታል ሆቴል ባህላዊ አዳራሽ ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ አካለወልድ አምዴ የኩባንያው የሽያጭ ዳይሬክተር እንደተናገሩት ኩባንያቸው በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማትን የባንኪንግ ሥርዓት እንዲዘምን ከዘጠኝ ባንኮች ጋር አብረን እየሠራን እንገኛለን ብለዋል።

ITSS ዋና መ/ቤቱ በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ ሲሆን በተጨማሪም በዓለም ዙርያ በአውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ አሜሪካ፣ አፍሪካ እና እስያ ጨምሮ 23 የስትራቴጂክ ቢሮዎች እንዳሉትም ጨምረው ገልጸዋል።

አይቲኤስኤስ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የባንክ አገልግሎቶችን እና ለባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በማቅረብ ላይ ይገኛል።

56030cookie-checkበጄኔቭ ሲውዘርላንድ ዋና ቢሮውን ያደረገው አይቲ ሶሉሽንስ ሰርቪስ ( ITSS) በኢትዮጵያ ቢሮውን ከፈተ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE