ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ያሰናዳው የአዲስ አመት ኤግዚብሽንና ባዛር « መርካቶን በሚሊንየም» በሚል ከፊታችን ነሀሴ 20 እሰከ ጷጉሜ 6 በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳወቁ።
የባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ዋና ስራ አስኪያጅ
አቶ ኤፍሬም ስዩም በመግለጫው መርሐግብር ላይ እንገለጹት «መርካቶን በሚሊንየም» በሚል ለተከታታይ 16 ቀናት በሚቆየው በዚህ የንግድ አውደ ርዕይ ላይ ከአንድ ሺህ በላይ የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ሀገር ኩባኒያዎች ፣ ሪል-እስቴቶች የፋይናንስ ተቋማት ፣ የምግብ እና የአልባሳት ምርት አቅራቢዎች ፣ የስጦታ እቃዎች ፣ የቤት እና የቢሮ መገልገያ በአጠቃላይ መርካቶ ውስጥ የሚገኙ እቃዎችን በአንድ ላይ የሚገኝበት የንግድ አውደ ርዕይ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በቀን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሸማቾች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።
በርካታ ፕሮግራሞችን በማሰናዳት ዝነኛ የሆነው ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር በሚያሰናዳው በዘንድሮ የአዲስ አመት የንግድ አውደ ርዕይ ላይ ገዥና ሻጭን፣ አምራች እና ሸማቹን በአንድ የሚያገናኝ ከመሆኑ ባሻገር ወቅታዊ የፍጆታ እቃ ንረትን እና የኑሮ ውድነት ከመቀነስ አንጻር የቅድሚያ የትኩረት እንደተሰጠበት በመግለጫው ላይ ተገልጿል።
በመዝናኛ ዝግጅቱ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን የገለጹት የሲሳይ አድሬሴ ፕሮሞሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ አድሬሴ ሸማቾች እና ጎቢኚዎች በመግቢያ ቲኬት ሽልማት የሚያገኙበትን ጨምሮ ልጆች ዘና የሚሉበት የማቆያና የጨዋታ ቦታ ፤ ነጻ ዋይፋይ እንዲሁም በየዕለቱ ዝነኛ አርቲስቶች የሚሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት እንደተዘጋጀ ገልጸዋል።
በዚህ በአይነቱ ለየት ያለ ባለው የንግድ አውደ ርዕይ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ድርጅቶች ፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ፈጥነው በመመዝገብ ለአጭር ጊዜ በሚቆይየው 10 በመቶ ቅናሽ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ በመግለጫው ተገልጿል።
(ጌች ሐበሻ)
???? Sisay Guzay
555600cookie-check«መርካቶን በሚሊንየም » የንግድ አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው።no