ኖርዝ ኢስት ትሬዲንግ የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አበሰረ።

Reading Time: 2 minutes
በምሥራቅ አማራ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥቅምን ላይ ለማዋል የሚያስችል ኖርዝ ኢስት ትሬዲንግ አክሲየን ማህበር የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳወቁ።

በምሥራቅ አማራ በወሎና ሸዋ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን ጥቅም ላይ ለማዋል ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አክሲዮን በመግዛት አሻራቸውን እንዳኖሩ የኖርዝ ኢስት ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር አደራጅ የቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ደሳለኝ ጥሪ በመግለጫው ላይ አሳውቀዋል።

አክሲዮን ማህበሩ በ16 ምሁራንና ባለሀብቶች አደራጅነት የተቋቋመ ሲሆን ፣ የሲሚንቶ ፣ ብረታ ብረት፣ የቢራ እና ዘይት ፋብሪካዎችን የማቋቋም ዕቅድ እንዳላው የቦርዱ ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ደሳለኝ የገለጹ ሲሆን አክሲዮን ማህበሩ በሸዋና በወሎ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን ጥቅም ላይ ከማዋል ባሻገር ለአካባቢው ማህበረሰብ ወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

ኖርዝ ኢስት ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ለ ልዩ አደረረጃጀቶችን በመፍጠር ፣ ጽህፈት ቤት በማቋቋም፣ የማዕድን የምርመራ ፈቃድ በመውሰድ፣ በአጋርነት አብሮ ሊሰሩ የሚችሉ አቅም ያላቸውን የውጭ ባለሀብቶች በማፈላለግ፤ የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን መስራት ውጤታማ የሆኑ አግባብ በማከናወን ወደ ተግባር ምዕራፍ ለማሸጋገር በሂደት ላይ እንደሚገኝ በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

የአክሲዮን ሽያጩ ዝቅተኛው አስር ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛ ደግሞ ሃምሳ ሚሊዮን ብር መሆኑን ኖርዝ ኢስት ትሬዲንግ
አክሲየን ማህበር አሳውቋል።

55500cookie-checkኖርዝ ኢስት ትሬዲንግ የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አበሰረ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE