ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ ለ2ኛ ጊዜ ሰልጣኞችን አስመረቀ።

Reading Time: 2 minutes
ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ ለሁለተኛ ጊዜ በድንገተኛ ሕክምና ቴክኒሻን ያሰለጠናቸውን 55 ሰልጣኞችን ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በመልካ ኢንተርናሽናል ሆቴል አስመረቀ።

ለሁለተኛ ዙር የሚያሰለጥናቸውን ተማሪዎች በድንገተኛ ሕክምና ቴክኒሻን ደረጃ 3 እና 4 ሲሆን ኮሌጁ ላለፉት 20 ወራት በንድፈ ሀሳብና በተግባር የታገዘ ስልጠና የድንገተኛ ሕክምናን ከአምቡላንስ ማሽከርከር በአንድነት ያጣመረ ወደፊት በሙያው ላይ ለሚቆዩ ፓራሜዲክ ለመሆን የሚያስችል ዕድል መፍጠሩን የጠብታ አምፑላንስ መስራች አቶ ክብረት አበበ በሰልጣኞች ምረቃ መርሐግብር ላይ ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት ለምረቃ ከበቁ ምሩቃን መካከል 26ቱ በአዲስ አበባ ከሚገኙ 5 ሆስፒታሎች የተመለመሉ በመሆኑ እነዚህ ሆስፒታሎች ሰልጣኞች የስልጠናው ተጠቃሚ እንዲሆን በመፍቀድ ሙሉ ደመወዛቸውን እየከፈሉ፣ በመደበኛ የቀን መርሐ ግብር ፕሮግራም አንዲማሩ በማድረግ በስራ ላይ ባይሆንም ጥቅማጥቅማቸው እንዳይቀርባቸው ከማድረጋቸውም በላይ ለተግባር ልምድ ፈቃደኛ በመሆን ስልጠናው ተግባር ተኮር እንዲሆን ላደረጉት ተቋማት የኮሌጅ ዲን አቶ ስለሺ ሞላ አመስግነዋል።

ጠብታ አምቡላንስ በግል ዘርፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ተቀዳሚ ተጠቃሽ ሲሆን ተቋሙ የቅድመ ሆስፒታል ላይ ትኩረት በመስጠት ጎን ለጎን የሰው ሀብት ልማቱም በተገቢው ሁኔታ ማጠናከር እንደሚገባ አፅንኦት በመስጠት በቅድመ ሆስፒታል ድንገተኛ ህክምና ባለሙያዎች (EMU) ስልጠና በሀገሪቱ እንዲጀመር ከጤና ሚኒስቴር ጋር በአጋርነት በመስራት በሀገሪቱ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስር በኦሮሚያ፣ አማራና ትግራይ ክልል ሲጀመር ከካናዳ የኢትዮጵያ የሀኪሞች ማህበር ጋር በመተባበር ልምድ ያላቸው የፓራሜዲክ ባለሙያ በማስመጣት በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ኮሌጅ የተቀረፀውን ስልጠና በመስጠት ኮሌጆቹ ወደ ስልጠና እንዲገቡ በማድረግ ረገድ የጠብታ አምቡላንስ ድርሻ የላቀ እንደሆነ የኮሌጅ ዲን አቶ ስለሺ ሞላ ገልጸዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሙልጌታ እንዳለ ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆኑትን የድንገተኛ ህክምና ቴክኒሻኖች አስመርቆ በጤናው ዘርፍ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ በማድረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በምረቃው መርሐግብር ላይ የክብር ተናጋሪ የሆኑት ሲስተር ተዋበች ኃይሌ ለተመራቂዎች ያላቸውን ልምድ እና ተሞክሮ ያቀረቡ ሲሆን ሠልጣኝ ተመራቂዎች በቅንነት በታማኝነት ሙያቸውን አክብረው እንዲሰሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

55480cookie-checkጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ ለ2ኛ ጊዜ ሰልጣኞችን አስመረቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE