ሂጅራ ባንክ የሀብት ምጣኔውን ሰባት ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን አሳወቀ።

Reading Time: < 1 minute
የሂጅራ ባንክ ዛሬ በስካይላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሳወቀው በተጠናቀቀው በጀት አመት የሀብት ምጣኔውን ሰባት ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን አሳወቀ።

ሂጅራ ባንክ ከብሄራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኘት በሀገራችን ሙሉ ለሙሉ ሸሪዓውን መሠረት ያደረገ የወለድ አልባ አገልግሎት ለመስጠት ነሐሴ 29 ቀን 2013ዓ.ም ሥራውን መጀመሩ ባሳለፈው የአንድ ዓመት ከአስር ወር ጉዞ በሀገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ አመርቂ የዕድገት መጠን በማስመዝገብ በስኬት ጎዳና እየገሰገሰ እንደሚገኝ የገለጸ ሲሆን በተጠናቀቀው የ 2022/23 የበጀት ዓመት 162% (አንድ መቶ ስድሳ ሁለት በመቶ) የትርፍ መጠን ዕድገትን ጨምሮ በርካታ አንኳር ስኬቶችን ማስመዝገቡን በዛሬው መግለጫ ላይ አሳውቃል።

ሂጅራ ባንክ የጥቅል ትርፍ መጠኑን በ 162 በመቶ ፣ የደንበኞቹን ብዛት በ 122 በመቶ ፣ የተቀማጭ ገንዘቡን በ 273 በመቶ ፣ የሀብት መጠኑን በ 207 በመቶ ፣ የቅርንጫፎቹን ብዛት 80 በመቶ ፣ ዓመታዊ ገቢውን በ 1,442 በመቶ ማሳደጉን አሳውቃል።

ሂጅራ ባንክ እነኚህን ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ማስመዝገብ የቻለው ባጠቃላይ የባንክ ኢንዱስትሪው በከፍተኛ ዉድድር ላይ ባለበትና እንዲሁም እንደ ሀገር በኢኮኖሚው ዘርፍ ከፍተኛ ጫና በሚስተዋልበት ወቅት መሆኑ ስኬቱን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል ተብሎ ተገልጿል።

55350cookie-checkሂጅራ ባንክ የሀብት ምጣኔውን ሰባት ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን አሳወቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE