የሬዲዮ ፕሮግራም አቅራቢዋ ድርሻዬ ዳና (ድርሹ ዳና) በሦስት ሚሊየን ብር ለሶል ሻሎም ፈርኒቸር የሁለት ዓመታት የማስታወቂያ አምባሳደር ለመሆን ተፈራረመች።
ከሰባት ዓመታት በፊት እንደተመሰረተ የተገለፀው ድርጅቱ የተሻሉ ስራዎችን ለመስራት በማሰብ የሬዲዮ ፕሮግራም አቅራቢ የሆነችው ድርሹ ዳና በራሷ መንገድ ራሷን የሆነች፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በብልሃት ያለፈች፣ በማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ መፍጠር የቻለች፣ ሳቂታ በመሆኗ፣ በግሏ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ስትሰራ የቆየች በመሆኗ ድርጅቱ የክብር አምባሳደር አድርጓት እንደመረጣት ተገልጿል።
ድርሹ ዳና በበኩሏ “ምርጫችሁ ስለሆንኩ ደስ ብሎኛል፣ ለሁለት ዓመታት ለመስራት ተስማምቻለሁ፣ ለሁለት ዓመታት ስራዎች ሦስት ሚሊዮን ብር ተከፍሎኛል “ብላለች።
ድርሹ ዳና በእጇ በሚገኙ የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆቿ ፣ቢልቦርዶች ፣ የጋዜጣና መጽሔት፣ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች ላይ ሶል ሻሎም ፊርኒቸርን በመወከል ለሁለት ዓመታት ታገለግላለች።
ሶል ሻሎም ፈርኒቸር የእንጨት ስራና ውጤቶችን በሀገር ውስጥ ለበርካታ ባንኮች፣ ሆስፒታሎች፣ ት/ቤቶች፣ መንግስታዊ ለሆኑና ላልሆኑ ተቋማት በማቅረብ የታወቀ ሲሆን በአዲስ አበባ አራት ቅርንጫፍዎች አሉት በቅርቡም በክልል ከተሞች ሌሎች ቅርንጫፎችን ለመክፈት እንደታሰበ ተገልጿል።
552700cookie-checkድርሹ ዳና የሶል ሻሎም ፈርኒቸር አምባሳደር ሆነችno

- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን