ዲቤክ ለታዳጊዎች ልዩ የክረምት ስልጠና መስጠት ሊጀምር ነው።

Reading Time: 2 minutes
“መልካም ዕውቀት በክረምት” በሚል መሪ ሐሳብ ልዩ የልጆች የክረምት ሥልጠና ከመጪው ሐምሌ 1 ቀን 2ዐ15 ጀምሮ ለሁለት ወራት ያህል መስጠት ሊጀምር መሆኑን ዲቤክ ዓለም አቀፍ የእውቀት ማዕከል ዛሬ ሴኔ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ለመጡ የሚዲያ ተቋም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳውቀዋል።

የስልጠናው ይዘት እና አላማ ያብራሩት የዲቤክ ዓለም አቀፍ የእውቀት ማዕከል መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቤዛ አበራ እንደገለጹት ልጆች የነገ አገር ተረካቢ እንደመሆናቸው መጠን በእውቀት፣ በሥነ-ልቦናና ተግባቦት ክህሎቶች የታነጹ ብቁ ዜጎች እንዲሆኑ፤ ጥራት ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲያገኙ ዲቤክ እየሰራ መሆኑን ገልጸው በመጪው ሁለት የክረምት ወራት የልጆች ዕውቀት ፣ ዝንባሌ እና ክህሎት ላይ የተመሠረተ ስልጠናዎችን በአዲስ አበባ በሚገኙ ሶስት የተመረጡ ቦታዎች ማለትም ቦሌ ፣ ብስራተ ገብርኤል እና ፒያሳ አካባቢ ላይ ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ዲቤክ ዓለም አቀፍ የእውቀት ማዕከል ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራሞችን ማለትም፤ በፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ሜታ ፊዚክስ፣ ሥነ ፈለግ ፣ ማቲማቲክስ ፣ በልጆች ሥነልቦና ፣ በዕውቅት ዕድገት ፣ ፕሮግራሚንግ እና በሌሎች የተለያዩ የዕውቀት እና የተግባቦት ክህሎቶች ላይ ልጆች በቂ ግንዛቤና እውቀት እንዲኖራቸው በማሰብ ልዩ የልጆች የክረምት ሥልጠና አዘጋጅቷል።

ሥልጠናው ከስምንት ዓመት ጀምሮ እስከ 18 ዓመት ድረስ ላሉ ልጆች የሚሰጥ ሲሆን፤ በሀገራችን ዕውቅ ዩንቨርሲቲዎች ውስጥ የሚያስምሩ ምሁራን እና የሕጻናት ሥነ ልቦና ባለሙያዎች ሥልጠናዎቹን ለመስጠት በዝግጅታችሁ ላይ መሆኑን በመግለጫው ላይ ገልጸዋል።

ዲቤክ ዓለም አቀፍ የእውቀት ማዕከል ከተመሠረተበት ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ፤ በአለም ዙሪያ ላሉ ሕጻናት ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት፣ እድሜ ልክ የሚቆይ የመማር ፍላጎትን እንዲያዳብሩ እና ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅምው የነገ ብቁ አገር ተረካቢዎች እንዲሆኑ ማድረግን ዓላማ ይዞ በመስራት ላይ ይገኛል።



55190cookie-checkዲቤክ ለታዳጊዎች ልዩ የክረምት ስልጠና መስጠት ሊጀምር ነው።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE