ሕክምናውን ከስልጠና ጋር ለማስጀመር በእስራኤል ሀገር የሚገኘው “ኢንፊ” ተቋም ከኢትዮ-ኢስታንቡል ጄነራል ሆስፒታል፣ ከጤና ሚኒስቴርና ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጋር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡ሕክምናው በኢትዮጵያ ሲጀመር ከ5 እስከ 60 ዓመት ለሆናቸው ወገኖች አገልግሎቱ እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሚጥል በሽታ ታማሚዎች 70 በመቶ ያህሉ በመድኃኒት ሕክምና የማይድን በመሆኑ የቀዶ ጥገና ሕክምናው ያስፈልጋቸዋል መባሉን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ÷ የሕክምናው መጀመር ኢትዮጵያን “በኒውሮሞዱሌሽን” ሕክምና ዘርፍ አንድ እርምጃ ወደፊት ያራምዳል ብለዋል፡፡ ለሕክምናው ባለሙያዎችን በማሰልጠንና በምርምር ከአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ የሕክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በጥምረት እንደሚሰሩ ጠቁመዋል፡፡የሚጥል በሽታ ቀዶ ሕክምናውን በቀጣዩ አመት በጥር ወር ለመጀመር እቅድ ተይዟል፡፡ከሚጥል በሽታ በተጨማሪ እንደ ፓርኪንሰን ያሉ የነርቭ በሽታዎች ሕክምናም ይሰጣልም ነው የተባለው፡፡