የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ስርጭት በሃምሌ ወር እንደሚጀምር አስታወቀ

Reading Time: < 1 minute

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ስርጭት በመጪው ሃምሌ ወር ለመጀመር እቅድ መያዙን አስታውቋል።ድርጅቱ የእርዳታው ተጠቃሚዎች በምን መልኩ እንደሚመረጡ ከፍተኛ ቁጥጥር ካደረገ በኋላ በሚቀጥለው ወር የምግብ ዕርዳታ ስርጭቱን ዳግም ለመጀመር ማቀዱን፤ የድርጅቱ ከፍተኛ ባለስልጣን ነግረውኛል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።ባለስልጣኑ “የአለም ምግብ ፕሮግራም የእርዳታው ተጠቃሚዎችን በመምረጥ ሂደት ውስጥ የበለጠ ቀጥተኛ ተሳትፎ ሊኖረው ይገባል “ያሉ ሲሆን፤ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት አዎንታዊ ግብረ መልስ ከተገኘ በኋላ፤ በትግራይ እና ለስደተኞች ካምፖች የሚያርገውን እርዳታ በሃምሌ ወር አጋማሽ ላይ ሊቀጥል እንደሚችል አመላክተዋል።ኢትዮጵያ ውስጥ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ለዚህም ምክንያቱ በአፍሪካ ቀንድ ባለፉት አስርት ዓመታት የተከሰተው አስከፊ ድርቅ እና በትግራይ ለኹለት ዓመታት የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት መሆኑ ተመላክቷል።የአለም ምግብ ፕሮግራም ከእነዚህ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ውስጥ፤ ወደ 6 ሚሊዮን ለሚጠጉ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ሲሰጥ መቆየቱን አስታውቋል።ድርጅቱ በትግራይ ክልል በግንቦት ወር በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ደግሞ በሰኔ ወር “የእርዳታ እህል ስርቆት ተበራክቷል” በሚል ምክንያት የምግብ ድጋፉን ማቋረጡ ይታወሳል።
54940cookie-checkየአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ስርጭት በሃምሌ ወር እንደሚጀምር አስታወቀ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE