በጎ አድራጊዋ ጋዜጠኛ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።

Reading Time: 2 minutes
በጎ አድራጊዋ ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ በማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ያሰባሰበችውን ከሃምሳ ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።

ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ ላለፉት አራት አመታት “ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ” በሚል መሪ ሐሳብ የልደት ቀኗን ምክንያት በማድረግ ለኢትዮጵያ የልብ ህመም መርጃ ማዕከል ገቢ በማሰባሰብ በተለያዩ ጊዚያት ህጻናትን ስታሳክም የቆየች ሲሆን ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ግምቱ ከሃምሳ ሚልዮን ብር በላይ የሆነ ከ140 አይነት በላይ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በተወካይ አማካኝነት ለማዕከሉ ድጋፍ አድርጋለች።

ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ ይህንን የበጎ አድራጎት ስራ ለማጠናከር ” ላይ ፎር አፍሪካ ” የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአሜሪካን ሃገር ያቋቋመች ሲሆን በዛሬው እለት የተደረገው ድጋፍ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ላደረጉት ግለሰቦች እና ተቋማት በተለይም ደግሞ ተቀማጭነቱ በአሜሪካ ላደረገው ” ፕሮጀከት ኪዬር” ጋዜጠኘዋ በተዋካያ ጋዜጠኛ የኃለሸት ዘሪሁን በኩል ምስጋናዋን አቅርባለች።

የልብ ቀዶ ህክምና እና የደም ስር ውስጥ ህክምና በሀገራችን የሰፈው መሰጠት ያልተጀመረ አገልግሎት ከመሆኑ አንጻር፣ እንዲሁም የሚያስፈልጉት ጥሩ እቃዎች እና መድሀኒቶች በአይነታቸው ዘርፈ ብዙ እና ዋጋቸውም ከፍተኛ በመሆኑ ጥሬ ገንዘብ ቢኖር እንኳን በሀገራችን ውስጥ እንደልብ ማግኘት ከባድ መሆኑን የገለጹት የማዕከሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ህሩይ ዓሊ ጋዜጠኛዋ ላደረገችው መልካም ተግባር በማዕከሉ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ርክክብ መርሐግብር ላይ እንደተገለጸው ማዕከሉ በሀገሩቱ በጠቅላላ የሚላኩ ታካሚዎችን የሚያሰተናግድበት ብቸኛ ተቋም በመሆኑ በአሁኑ ሰአት ከ7000 በላይ ቀዶ ህክምና የሚጠባበቁ ህጻናትና ታዳጊዎች የሰዎችን ድጋፍ እየተጠባበቁ ይገኛሉ ተብላል።

(ጌች ሐበሻ)

54790cookie-checkበጎ አድራጊዋ ጋዜጠኛ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE