በጨረታ ሂደት ላይ ከጉቦ እና ከመሰል የስነምግባር ችግሮች ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን ያቃልላል የተባለው ይህ አሰራር የሰዎችን ንክኪ በእጅጉ እንደሚቀንስ ተሰምቷል!
ኦክሽን ኢትዮጵያ በተባለ ተቋም የተዋወቀው አሰራሩ የመንግስት ተቋማት፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ አለማቀፍ ድርጅቶች እና የግል ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች በጨረታ መሸጥ የፈልጉትን ንብረቶች በዲታጂታል መንገድ ቀላልና ምቹ ሆኖ ለተጫራቾች ተደራሽ እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
እንዲሁም ተጠቃሚዎች የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው ጊዜና ገንዘባቸውን ሣያባክኑ ካሉበት ቦታ ብቻ ሆነው በስልካቸው ወይም በኮምፒዉተራቸው ጨረታን መጫረት ያስ4ችላል ተብሏል
በመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ በግል ተቋማት ቀድሞ ይከናወን የነበረው የጨረታ ሂደት እጅግ አድካሚ፣ ጊዜና ገንዘብን የሚያባክን ግልፅ ያልሆነና የተደራሽነት ዉስንነት ያለበት በመሆኑ እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ ሚና ይኖረዋል ነው የተባለው፡፡