ሶስተኛው “ጣፋጭ ሕይወት ሽልማት” በድምቀት ተካሄደ።

Reading Time: 2 minutes
ሶስተኛው ስሶተኛው “ጣፋጭ ሕይወት ሽልማት” ትናንት ማምሻውን በቤልቪው ሆቴል በማህበረሰባችን ላይ መልካም አሻራ እያሳረፉ የሚገኙ ግለሰቦች እና ተቋማትን የእውቅና እና የምስጋና መርሐግብር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተካሄደ።



ላለፉት ሁለት አመታት በተከታታይ በግንቦት ወር መጨረሻ የሚከናወነው “ጣፋጭ ሕይወት ሽልማት” ትናንት ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም በስራ ፈጠራ ፣ በአነቃቂ ንግግር፣በበጎ አድራጎት ፣ዝናን ለመልካም ምግባር ፣ ሚድያውን ለስነልቦና ግንባታ እና ማህበራዊ ሚድያውን ለመልካምነት የተጠቀሙትን ግለሰቦች እና ድርጅቶች አመስግነዋል እውቅና ሰጥተዋል።

ግንቦት 30 የምስጋና ቀን እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን « የእኔ ነኝ መፍትሔው» ኘሮጀክት ሀሳብ አመንጪ እና የጣፋጭ ህይወት የራዲዮ ኘሮግራም እና ሽልማት ዋና አዘጋጅ አቶ አንተነህ ተስፋዬ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግር ያደረጉ ሲሆን የእኔ ነኝ መፍትሔው ጨምሮ ሶስተኛው የጣፋጭ ህይወት ሽልማት ኘሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ ትልቅ ድርሻ ላበረከቱ ተቋማት እና ግለሰቦች እንዲሁም በጎ ፍቃደኞች ምስጋናቸውን አቅርቧል።

1.ስቴም ፓወር ኢትዮጵያ(በልዩ ተሸላሚ ዘርፍ ተሸላሚ)
2.አቶ ሸሀብ ሱሌማን (ተስፋ የሚጣልበት ስራ ፈጠራ ዘርፍ ተሸላሚ)
  1. ኢሳያስ ጋሻው (በስራ ፈጠራ ዘርፍ ተሸላሚ)
    4.ወጣት ሀና ሀይሉ(ተስፋ የሚጣልባት የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ ዘርፍ) ተሸላሚ
  2. አቶ አሸናፊ ታዬ (የህይወት ክህሎት ስልጠና በተግባር ዘርፍ ተሸላሚ)
    6.መቄዶንያ የአረጋውያንና አእምሮ ህሙማን ማዕከል(በዘንድሮው የጣፋጭ ህይወት ሽልማት በበጎ አድራጎት ዘርፍ ተሸላሚ ተቋም)
    7.አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ(ዝናን ለመልካምነት ዘርፍ ተሸላሚ)
    8.”ላይፍ ኢዝ ጉድ “የራዲዮ ፕሮግራም (ሚዲያን ለስነልቦና ግንባታ ዘርፍ አሸናፊ የራዲዮ ፕሮግራም )
    9.ዳጊ ሾው(ሚዲያውን ለስነ-ልቡና ግንባታ ሽልማት ዘርፍ ተሸላሚ የቴሌቪዥን ፕሮግራም)
    10.የእምዬ ማዕድ ለልጆቻችን(ማህበራዊ ሚዲያውን ለመልካም ተግባር የተጠቀመ ዘርፍ /በፌስቡክ ተሸላሚ/)
    11.ማስተር አብነት ከበደየዘንድሮው የጣፋጭ ህይወት ሽልማት ማህበራዊ ሚዲያውን ለመልካም ተግባር የተጠቀመ ዘርፍ /በዩቲዩብ ተሸላሚ/)
    12.ባለደራው (ማህበራዊ ሚዲያውን ለመልካም ምግባር በመጠቀም (ቲክቶክ)ተሸላሚ)

(ጌች ሐበሻ)
????Tekle Markon

54400cookie-checkሶስተኛው “ጣፋጭ ሕይወት ሽልማት” በድምቀት ተካሄደ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE