አዶልፍ ሂትለር የፓርኪንሰን ህመም ነበረበት!!

Reading Time: < 1 minute



ሂትለርን ማስተዋወቅ የሚያስፈልገው ግለሰብ አይደለም። ብዙ የአእምሮና የአካል ህመም እንደነበረበት ይጠረጠራል። ሂትለር በዘመኑ ከ90 በላይ የተለያዩ መድሀኒቶች ወስዶ ያውቃል። ለዛሬ የነርቭ ህመም የሆነው የፓርኪንሰን ህመም ምልክቶቹን አቀርባለሁ።

ወደ የአገዛዝ ዘመኑ መጨረሻ የተቀረፀ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ሂትለር ወታደሮችን በቀኝ እጁ ሰላም እያለ ግራ እጁ ሲንቀጠቀጥ ያሳያል። ይህ የእጅ መንቀጥቀጥ (Tremor) ከፓርኪንሰን ዋና ምልክት ሲሆን ሰላምታ እየሰጠ እያለ ቀኝ እጁ አለመንቀጥቀጡ (Resting tremor መሆኑ) ሌሎች እጅ መንቀጥቀጥ ከሚያመጡ ህመሞች ይልቅ ወደ ፓርኪንሰን ይጠቁማል። አረማመዱ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት አንስቶ ዝግ የማለት ሁኔታ (Shuffling gait) ነበረው።

በህይወቱ ፀሀይ መጥለቂያ አካባቢ ሲያክሙት የነበሩ ሁለት ሀኪሞች ፓርኪንሰን እንዳለበት ግምታቸውን አስቀምጠዋል። የፓርኪንሰን ህመም በዋናነት የነርቭ ህመም ነው። ይሁን እንጂ በተጓዳኝ የጭንቀትና የዲፕረሽን ህመሞች ሊያስከትል ይችላል።

የአእምሮ ህመም ሀብታም ደሀ፤ የተማረ ያልተማረ፤ ፖለቲከኛ ተራ ህዝብ ሳይለይ ማንም ሰው ላይ ሊከሰት የሚችል ህመም ነው።



©ዶ/ር ዮናስ ላቀው
54330cookie-checkአዶልፍ ሂትለር የፓርኪንሰን ህመም ነበረበት!!

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE