የምወድደው አለቃዬን ዛሬ አገኘሁት፣  ከዓመታት በኋላ።

Reading Time: < 1 minute

ያለፈውን ጊዜ አንስተን እንደ አዲስ ተሳሳቅን። በተለይ የሚከተለውን ገጠመኜን። ባንክ ተቀጥሬ አመት ያህል እንደሆነኝ አንድ እሁድ እለት ከጓደኞቼ ጋር ኳስ ለማየት ከቤት ወጣን። ይሁንና ኳስ እያየን ድራፍት እየጠጣን የነበርን ጎረምሶች ባላሰብነው ሁኔታ በከተማው የሚገኙ አንድ ባለሀብት ባስወረዱልን ውስኪ እስከ እኩለ ሌሊት ስንራጭ አመሸን።

ጠዋት ላይ አንድ ጓደኞዬ ቤት ስነቃ ፣ እራሴን መሸከም አቅቶኛል። ቤቱ በመጠጥ ሽታ ተሞልቷል። በእርግጠኝነት በእዚህ መልኩ ሥራ መሄድ እንደማልችል ስለገባኝ ወደ አለቃዬ ስልክ ደውዬ…

“ዘመድ ስለሞተ ለመቅበር ወደ ገጠር እየሄድኩ ስለሆነ ፍቃድ ፈልጌ ነበር…” ስል ፈቃድ ጠየቅኩ።

ተፈቀደልኝ።

መሀል ላይ ሌላ መስሪያ ቤት የሚሰራ ጓደኛዬም ከእንቅልፉ ነቅቶ ወደ ቢሮው ደውሎ ለቅሶ ገጥሞኛል በማለት ሥራ ካስፈቀደ በኋላ የእኔን ጠየቀኝ።

“እንዲህ ሀንጎቨር ሳይለቅቀኝ ሥራ ገብቼማ የመጠጥ ሽታ ስጋብዛቸው አልውልም። እኔም አለቃዬ ጋ ደውዬ ዘመድ ሞቶብኛል ብዬ ዋሸሁ። ጌታ ይቅር ይበለኝ!” አልኩት።

“እኔማ አሁን ላይ ዘመዶቼን በሙሉ ጨርሼ በጎረቤት ሞት ምናምን ማስፈቀድ ጀምሬአለሁ” አለኝ። ተሳሳቅን።

ይሁንና እየተሳሳቅን ሰዐት ለማየት ስልኬን ሳነሳ ሳላውቅ ነክቼው ኖሮ አለቃዬ ጋ ደውሎ እየቆጠረ አገኘሁት። በእርግጠኝነት ንግግራችንን ሰምቷል። ቆሌዬ ተገፈፈ፣ መሬት ተከፍታ እንድትውጠኝ ተመኘሁ። ነግቶ አለቃዬን እንዴት ፊቱን  እንደማየው ሲጨንቀኝ ዋለ፣ ማታም በሐሳብ ስገላበጥ፣ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ነጋ።

በማግስቱ ጭንቀት እየተጫጫነኝ፣ ልቤ እየደለቀ፣ አንገቴን ደፍቼ ወደ ምሰራበት ባንክ ሄድኩ። አለቃዬ እንደወትሮው በጠዋት ቢሮ ገብቷል። በጭንቀት እንደተዋጥኩ ፊቴን ከስክሼ ይቅርታ ለመጠይቅ ወደ እርሱ ሄድኩ።

ልክ እንዳየኝ ፊቱ ከንዴት ይልቅ በፈገግታ እንደተሞላ “ቀብር ደረስክ?!” ሲል ጠየቀኝ። ዝም አልኩ። ከፊቴ ላይ መሳቀቄን አንብቦ ነው መሰለ የእኔን ምላሽ ሳይጠብቅ…

“አይዞህ! አትጨነቅ። እኔም የሆነ ጊዜ ላይ እንዳንተው ጎረምሳ ነበርኩ። እረዳለሁ። ሌላ ጊዜ እንዳትዋሸኝ። አሁን ወደ ሥራህ ሂድ” አለኝ።
***


**


54250cookie-checkየምወድደው አለቃዬን ዛሬ አገኘሁት፣  ከዓመታት በኋላ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
Surafel

Surafel

Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly. Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly. Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly.
Surafel

Surafel

Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly. Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly. Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly.

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE